በአፈ/ከሳሽ ወ/ሮ ለምለም ፍሬው እና በአፈ/ተከሳሽ አቶ አደራ ቸኮል መካከል ባለዉ የጋብቻ ክርክር ጉዳይ በእንጅባራ ከተማ 05 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ ኮ/ር ዕድሜዓለም፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን መንገድ እንዲሁም በደቡብ ቻላቸው መኮነን መካከል የሚገኝ በአቶ አደራ ቸኮል ስም ተመዝግቦ የሚገኘውን የመኖሪያ ቤት/የድርጅት ቤት ንብረትነቱ የፍርድ ባለዕዳ የሆነው የሊዝ ዕዳ ያለበት በመነሻ ዋጋው ብር 3,367,344.08 (ሶስት ሚሊዮን ሶስት መቶ ስልሳ አባት ሺህ ሦስት መቶ አርባ አራት ብር 08 ሳንቲም) ስለሚሸጥ የጨረታ ማስታወቂያ ከጳጉሜ 02/2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 23/2019 ዓ.ም ድረስ በጋዜጣ በማዋል ጨረታው መስከረም 24/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 መሆኑን አዉቃችሁ ቦታዉ ድረስ በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ማሳሰቢያ:- ተጫራቾች ወደ ጨረታዉ ስትመጡ የጨረታዉን መነሻ ዋጋ ¼ ኛውን በሲፒኦ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት

