የልብስ ንድፍ

0
48

ጀርመናዊው የልብስ ንድፍ አውጪ ሲሞን ዊከርት በቁጥጥር ካሜራዎች (ሰርቪላንስ ካሜራ) ማንነትን መለየት የማያስችል ወይም የሚደብቅ የቀለም ቅብ ያለው ሸሚዝ መስራቱን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ ባለፈው ሳምንት  ለንባብ አብቅቶታል፡፡

የበጋ ሸሚዝ ንድፍ አውጪው ሰው ሰራሽ የቁጥጥር ካሜሪዎችን የሚያደናግር ማንነትን መለየት የማያስችል የተለያዩ ቅርፅ እና የቀለም ቅብን ነው አገልግሎት ላይ ያዋለው፡፡

መረጃውን ያካፈለው ድረ ገጹ እንዳሰፈረው ሲሞን ዋከርት የቅብ ንብብሮች፣ ጠርዞችን፣ ንፅፅሮችን እና የእጆች የእግር እና ከሰውነት ጋር ያላቸውን ምጥጥን በውል በመገንዘብ የቁጥጥር ካሜራን ድክመቶች የመለየት ስራን ከውኗል- ንድፍ አውጪው፡፡

“ዲጂታል ካምፉሌጅ” ሲል የሰየመው ሲሞን ዊከርት የነደፈው የሸሚዝ ቅብ የ“ኤ አይ” ስርዓቶችን በማደናገር ለባሹን ለመለየት እንዲያስቸግር አስቦበት የሰራው መሆኑ ነው የተብራራው፡፡

ከሁሉም በላይ አስገራሚው የሸሚዝ  የ”ቅብ የቀለም ንድፍ” ኤአይን በመጠቀም “አድርቨርስኤርያል ሉኘ” የተገላቢጦሽ ኡደትን በመገልገል የተሰራ መሆኑን ነው “ዴዚን” ለተሰኘ መጽሄት ያስረዳው – ሲሞን ዊከርት፡

ሲጠቃለል በክትትል ካሜራ ማንነትን መለየት የማያስችለው የሸሚዝ ቀለም ቅብ ንድፍ “ኤአይ”ን ራሱን መለየት የሚቸግረውን የቀለም ንድፍ በመጠየቅ የተሰራ መሆኑን ነው ሲሞን ዊከርት ያሰመረበት፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የመስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here