የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
36

የአዲስ ዘመን ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሠረት በ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ጨረታ የድርጅት 2 የመኖሪያ 2 በድምሩ 4 ቦታዎችን ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-

  1. መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ብቻ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይሆናል፡፡
  3. ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን በ11፡00 ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው የሚከፈተው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው ቀን 3፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን የሚከፈትበት ቦታ በተመለከተ በከተማ መሠረተ ልማት ጽ/ቤት ግቢ ከረፋዱ 3፡00 ይሆናል፡፡
  5. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 18 31 73 72 ወይም 09 37 81 60 41 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  6. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የአዲስ ዘመን ከተማ አስተዳደር መሬት አስተዳደር ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here