ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
39

የዜጎች ለዜጎች (Citizens to Citizens – C2C) ድርጅት በሚያስተባብረው የማህበረሰብ ፕሮጀክት ሥር በታች ጋይንት እና ሰዴ ሙጃ ወረዳዎች የሚገኙ ተጠቃሚ የማህበረሰብ ቡድኖችን በመወከል 6,000 ኩንታል እህል ከአንድነት የዘር ልማት ዩኒየን እንዲገዛ ስለተደረገና በአሁኑ ወቅት ከደብረ ታቦር ከተማ ወደ ታች ጋይንት ወረዳ እና ሰዴ ሙጃ ወረዳ የሚገኙ ቀበሌዎች ለማጓጓዝ የሚያስፈልገውን የማጓጓዣ አገልግሎት ለመግዛት ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን፣ ብቁ እና ልምድ ያላቸውን የትራንስፖርት ድርጅቶች ወይም ግለሰብተጫራቾችን በጨረታ ይፈልጋል፡፡

  1. የሥራው ዝርዝር
  • የሚጓጓዘው እቃ፡ እህል: በቆሎ
  • ጠቅላላ መጠን፡- 6,000 ኩንታል
  • የመነሻ ቦታ፡- አባ አረጋዬ አንድነት የዘር ልማት ዩኒየን፣ ደ/ጎንደር ዞን፤ ደብረ ታቦር ከተማ
  • የመዳረሻ ቦታዎች፡ በደቡበ ጎንደር ታች ጋይንት ወረዳ አርብ ገበያ ከተማ እና ቀበሌዎች ማዕከል እንዲሁም  በሰዴ ሙጃ ወረዳ፣ ሮቢት ከተማ ድረስ፡፡
  • ተጫራቾች የማጓጓዣ ዋጋቸውን በኩንታል ወይም በጠቅላላ መጠን መሠረት በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ የመዳረሻ ከተሞች እና ቀበሌ ማዕከል (በአማራጭ) በመጥቀስ ማቅረብ ይችላሉ፡፡ (ደ/ታቦር – አርብ ገበያ- ቀበሌ፡፡ ደ/ታቦር- አርብ ገበያ እና ደ/ታቦር – ሮቢት ከተማ፡፡
  1. የተጫራቾች መስፈርቶች
  1. የ2019 ዓ.ም. (2026/27) የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. የቲን ሰርተፊኬት ቅጅ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. የቫት ምዝገባ ማስረጃ (ተፈጻሚ ከሆነ) ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. በተመሳሳይ የእህል ወይም የእቃ ማጓጓዣ ሥራ ያላቸውን ልምድ ማሳየት አለባቸው፡፡
  5. እያንዳንዱ ተሽከርካሪ ቢያንስ 100 ኩንታል የመጫን አቅም ያለው መሆን አለበት፡፡
  6. የተሽከርካሪዎችን የሊብሬ ቅጅ እና የባለቤትነት ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. የግብር እዳ አለመኖሩን የሚገልጽ ማስረጃ ቢቀርብ ይመረጣል፡፡
  1. የጨረታ ሰነድ አቀራረብ
  2. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን እና የድርጅት ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. በኤንቨሎፑ ላይ “ለ6,000 ኩንታል እህል ማጓጓዣ አገልግሎት ጨረታ” ተብሎ በግልጽ እንዲጻፍ ይጠየቃል፡፡
  4. የቀረበው ዋጋ ሁሉንም ወጪዎች (ነዳጅ፣ ታክስና ሌሎች ተያያዥ ወጪዎች) ያካተተ ሲሆን ከደ/ታቦር አርብ ገበያ ከተማ እና ከከተማ ወደ ቀበሌ 40 ኪ/ሜ ለማደርስ በተናጠል እና የሰዴ – ሙጃ ሮቢት ከተማ ድረስ ተብሎ እንዲሞላ፡፡
  5. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ
  1. ጨረታው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ 5 የሥራ ቀናት ክፍት ይሆናል፡፡
  2. የጨረታ ሰነዶች በመጨረሻው ቀን ከቀኑ 11፡00 በፊት መቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ጨረታው በዚያው ቀን በተገኙ ተወዳዳሪዎች ፊት ይከፈታል፡፡
  1. አጠቃላይ ሁኔታዎች
  • አሸናፊው ተጫራች ሥራውን በተወሰነው ጊዜ እና በተፈለገው ጥራት ሊያከናውን ይገባል፡፡
  • ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱን የተጠበቀ ነው፡፡
  • ዝቅተኛ ዋጋ ብቻ የአሸናፊነት መለኪያ አይሆንም፤ የቴክኒክ ብቃትና ልምድም ይታያል፡፡

አድራሻ፡- የዜጎች ለዜጎች (C2C)፤ ባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት፤ ኖክ ሃቂቃ ህንጻ በአካል በመቅረብ ወይም ስልክ፡ 09 18 71 95 47 በመደወል ወይም ኢ-ሜይል፡ info@c2cethiopia.org መላክ ይችላሉ፡፡

የዜጎች ለዜጎች (Citizens to Citizens – C2C) ድርጅት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here