ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ደማ/01/2019 የጨረታ ዙር 1ኛ፤የጨረታ ዓይነት መደበኛ

0
36

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መሬት ቢሮ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004፣ አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከ”ሀ”  እስከ “ሠ” በተዘረዘረው መሰረት ለመኖሪያ እና ንግድ አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልፅ  ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በመክፈል ከአገልግሎት አቅርቦት ተጠሪ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በስራ ሰዓት መግዛት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ በ10ኛው ቀን የጨረታ ሰነድ የሚሸጠው እስከ ቀኑ 10፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
  3. የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸገው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ኛው ቀን 11፡00  ነው፡፡
  4. ቦታውን መጎብኘት ለምትፈልጉ ተጫራቾች የጉብኝት ፕሮግራም በውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
  5. ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00  በመምሪያው ግቢ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፤ 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  6. ስለጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ የተጫረቱበትን የቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘውን ዉጤት ከሀያ በመቶ ያላነሰ በዝግ አካውንት በማስገባት በባንክ የተመሰከረለት ሰነድ ከዋጋ እና የሃሳብ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. በጨረታው ለተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተመላሽ የሚደረገው የጨረታው አሸናፊ ከተረጋገጠበት ከሚቀጥለው ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ይሆናል፡፡
  9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
    የደብረ ማርቆስ ከ/አስ/መ/መምሪያ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here