የአካበቢ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
80

ወጣት መር እና አገር በቀል ድርጅት ተሳትፎ ለዘላቂ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፕሮግራም በአማራ ክልል (Y_SYEPA) በአማራ ልማት ማህበር (አልማ) እና በወጣት መር እና አገር በቀል ድርጅቶች የሚተገበር ፕሮግራም ነው፡፡ በመሆኑም የሊቦ ከምከም ወረዳ ወጣቶች ማህበር በሊቦ ከምከም ወረዳ እና በአዲስ ዘመን ከተማ ለወጣት ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች ፣ ከስደት ተመላሾች እና በሀገር ውስጥ ለተፈናቀሉ ወጣቶች የስራ ዕድል እና የገቢ ማስገኛ ተጠቃሚ ለማድረግ የበግና የፍየል እርባታና ማድለብ እንዲሁም ለእርባታና ማድለብ  የሚያገለግሉ ግብዓቶችን በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶችን በማወዳደር  በግልጽ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. የተጨማሪ አሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋገግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል አዲስ ዘመን ከተማ በሚገኘው የሊቦ ከምከም ወረዳ ወጣቶች ማህበር ቢሮ ቁጥር 01 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) የሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋጋጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች በማህበሩ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ያለምንም ስርዝ ድልዝ በትክክል በመሙላት አንድ ወጥ በሆነ ኢንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው፡፡
  7. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በሊቦ ከምከም ወረዳ ወጣቶች ማህበር ቢሮ ቁጥር 01 ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ላይ ይታሸጋል፡፡ በእለቱ በ8፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቻው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  8. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 54 66 77 / 09 87 99 74 94 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የሊቦ ክምከም ወረዳ ወጣቶች ማህበር

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here