ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
109

የሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሎት 1. የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2. ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት 3. የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 4. የመኪና መለዋዋጫ ዕቃዎች፣ ሎት 5. አነሰተኛ የእጅ መሳሪያ፣ ሎት 6. ህትመት እንዲሁም ሎት 7. ቋሚ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡- ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በስራ ዘርፍ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡ የማስጫኛ እና የማውረጃ ወጭዎችን በመሸፈን ሰ/ወሎ/ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የፎቶ ኮፒና የፋክስ ቀለሞች የኮምፒውተር ወረቀት እና እስኪሪቢቶዎች ኦርጅናል ለመሆናቸው ለሚወስደው ፕሪንተር ማስሞከር የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በባለሙያ ማስፈተሽ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ውድድሩ በድምር ዋጋ በሎት መሆኑ ታውቆ በየሎቱ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ዋጋ ሁሉንም ከነቫቱ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የጨረታ ሰነዱ ኦርጂናልና ኮፒው ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት በጨረታ ሰነዱ ከተዘረዘሩት እቃዎች 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
  6. ተጫራቾች ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች ማቅረብ አለባቸው፤ ባቀረቡት ዕቃዎች ላይ የጥራት ችግር ቢፈጠር የመመለስ /የመቀየር/ ግዴታ አለባቸው ይህ ካልሆነ በህግ ፊት ይጠየቃሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የሚገጣጠሙ እቃዎችን የመግጠምና የመግጠሚያ ወጭዎችን እራሳቸው ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ኮምፒውተር፣ ወንበሮች እና ፕሪንተር ወ.ዘ.ተ፣
  8. ከጨረታ ሰነዱና ከታሸገው ፖስታ ላይ የድርጅቱ ማህተም፣ የድርጅቱ ተወካይ ስምና ፊርማ ተነባቢ በሆነ መልኩ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡
  9. ያሸነፉበት እቃ ድምር ብር 20‚000 (ሃያ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ 3 በመቶ ተቀንሶ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  10. በተጨማሪም አሸናፊው ድርጅት ግብይት ከብር 20‚000 (ሃያ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ 7.5 ቫት ተቀንሶ ለመንግሰት ገቢ ይሆናል፡፡
  11. ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 39 በመምጣት ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት ዓይነት በመክፈል መውሰድና ማስገባት ይችላሉ፡፡
  12. ተጫራቾች የሞሉትን እቃ ድምር ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ቅድሚያ በባንክ በተመለሰከረ (ሲፒኦ) ያስያዙትን ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ አድርገው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  13. ተጫራቾች በጨረታው ለእያንዳንዱ እቃ የሚያስይዙት የገንዘብ መጠን ለአላቂ የጽህፈት መሳሪያ ብር ብር 3,900 (ሶስት ሽህ ዘጠኝ መቶ ብር)፣ ለኤሌክትሮኒክስ ብር 4,300 (አራት ሽህ ሶስት መቶ ብር)፣ ለቋሚ እቃ ብር 2,300 (ሁለት ሽህ ሶስት መቶ ብር)፣ ለጽዳት እቃዎች ብር 1,500 (አንድ ሽህ አምስት መቶ ብር)፣ ለመኪና እቃ ብር 6,500 (ስድስት ሽህ አምስት መቶ ብር)፣ ለአነስተኛ የእጅ መሳሪያ ብር 200 (ሁለት  መቶ ብር) እንዲሁም ለህትመት ስራዎች ብር 1,500 (አንድ ሽህ አምስት መቶ ብር) እና በላይ መሆን አለበት፡፡
  14. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ማስተካከያ ጥያቄ ካላቸው ከጨረታው መክፈቻ ጊዜ ከ5 ቀን በፊት ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  15. የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸገው ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ ቀከኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን በጨረታው ላይ ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታው ሲከፈት በግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 144/2018 መሰረት ተገዥ ይሆናሉ፡፡ የመቀበል ግደታ አለባቸው፡፡ ነገር ግን የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከሆነ የሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
  16. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከታሽገ በኋላ ማንኛውንም ማስረጃም ሆነ ጥሬ ገንዘብ በእጅ ይዞ መቅረብ አይፈቅድም፡፡
  17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ ይሆናል፡፡
  18. ተጫራቾች በጨረታው ሁለትና ከሁለት በላይ የሆኑ ተጫራቾች እኩል ነጥብ ካመጡ አሸናፊው በእጣ የሚለይ ይሆናል፡፡
  19. በጨረታው አሸናፊው ድርጅት ካሸነፈ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው እራሱን ማግለል አይችልም፡፡
  20. ለበለጠ መረጃ ለመጠየቅ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 033 331 14 34 በመደወል ወይም ሰሜን ወሎ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 39 በመምጣት መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሰሜን ወሎ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here