በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ውስጥ የሚገኘውን ቁርጥራጭ ብረታ ብረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡- ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፣ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸውጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ግዥውን ግምታዊ ዋጋ መሰረት በማድረግ ብር 50,000 (አምሳ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ (ሲፒኦ) በኮሌጁ ስም ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ መቆያ ጊዜ ከመስከረም 25/2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 09/2019 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ብቻ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆኑ የጨረታ መወዳደሪያውን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግዥ ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ16ኛው ቀን ማለትም ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም ሲሆን ከረፋዱ 4፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ጨረታው የሚከፈት ሁኖ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ውል ከያዘ በኋላ የሚጠበቅበትን ክፍያ በመክፈል ንብረቱን መረከብ ይኖበታል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት (ግለሰብ) ማሸነፉን በተገለፀ ከአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል ካልያዘ የጨረታ ማስከበሪያው ውርስ ይሆናል፡፡
- ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተገለፁ ነገሮች ካሉ በግዥ መመሪያው መሰረት ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡
- አሸናፊ ድርጅቱ (ግለሰቡ ) የሚዛን እና ሌሎች ወጭዎች በራሱ ሂሳብ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ኮሌጁ ግ/ፋ/ን /አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 774 07 71 ደውሎ ወይም በአካል ቀርቦ ማየት ( መረዳት) ይችላሉ፡፡
የቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

