የጨረታ መለያ ቁጥር: STARTUP-MAT-2026-0817-V12
የአማራ ነጋዴ ሴቶች ማህበር የሊቦ ከምከም ነጋዴ ሴቶች ማህበር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) ማስተርካርድ ፋዉንዴሽን በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ እየተተገበረ በሚገኘዉ የፀሃይ ታዳሽ ሃይል ለወጣቶች የስራ ፈጠራ ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች አገልግሎት የሚዉል የሶላር ኤሌክትሪካል እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች አሟልተው እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት (ቲን) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የምስክር ወረቀት ከዋጋ ማስታወቂያ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ወይም በማስታወቂያ ቦርድ መወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአማራ ነጋዴ ሴቶች ማህበር የሊቦ ከምከም ነጋዴ ሴቶች ማህበር ቢሮ (አዲስ ዘመን ፖሊቴክኒክ ግቢ ውስጥ) ወይም ባሕር ዳር ቀበሌ 14 አልዋቅ ሆቴል ጀርባ በሚገኘዉ አማራ ክልል ነጋዴ ሴቶች ማኅበር ዋና ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ7ኛው ቀን ከቀኑ 9፡30 ተዘግቶ በእለቱ ከቀኑ 10፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን እና የተጠየቁ ህጋዊ ሰነዶችን በማዘጋጀት በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጽሕፈት ቤቱ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በቦታው መገኘት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በሌሉበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 34 55 58 96 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የተቋሙ አድራሻ:- በአማራ ነጋዴ ሴቶች ማህበር የሊቦ ከምከም ነጋዴ ሴቶች ማህበር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት (አዲስ ዘመን ፖሊቴክኒክ ግቢ ውስጥ) ነው፡፡
በአማራ ነጋዴ ሴቶች ማህበር የሊቦ ከምከም ነጋዴ ሴቶች ማህበር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

