ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
70

የቢቡኝ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ግብዓቶች ማለትም የደን ዘር፣ የደጋ ፍራፍሬ፣ ፖሊተሊን ቲዮብ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች  መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ፈቃድ እና የንግድ ስራ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ወይም ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ (ቲን) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  3. የተለያዩ ግብዓቶች ማለትም ሎት 1. የደን ዘር (ጌሾ 150 ኪ/ግ፣ ግራቪሊያ 40 ኪ/ግ እና የፈ/ጽድ 40 ኪ/ግ) ሁኖ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እና ከኳራንታይን የጥራት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ሎት 2. የደጋ ፍራፍሬ (የአፕል መሰረተ ግንድ በቁጥር 25,000 (ሀያ አምስት ሽህ) ዝርያው mm106) ሁኖ የችግኙ ቁመት 1.3 ሜትር ተስተካክሎ ቀጥ ብሎ የወጣ፣ የችግኙ ውፍረት ከእርሳስ ቅርጽ ያላነሰ ወይም ያልወፈረ፣ ችግኙ በሁሉም አቅጣጫ ስር ያለው፣ ከበሽታና እና ተባይ የፀዳ እና ከኳራንታይ የጥራት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ሎት 3. ፕላስቲክ ወይም ፖሊቲን ቲዩብ 3 ኩ/ል ዲያሜትሩ ባለ 10 ሴ/ሜ እና ነጭ የሆነ መሆን አለበት፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች  ፎቶ ኮፒ፣ የአሰሪው መ/ቤት እና የተጫራቾች  ሙሉ ስም፣ አድራሻ ፣ ፊርማ ፣ ማህተም  በማስቀመጥ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት በእያንዳንዱ ሰነድ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) የማይመለስ  በመክፍል ከቢ/ወ/ገ/ኢ/ጽ/ቤት ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃው ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ)  ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢ/ወ/ግ/ጽ/ቤት/በብ/የሚ/የግ/ግ/ክ ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት  ከመስከረም 25/2019 ዓ/ም እስከ ጥቅምት 4/2019 ዓ/ም 10፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚሁ ቀን 10፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡
  8. ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግብርና ጽ/ቤት/በብ/የሚ/የግ/ግ/ክ ቡድን ቢሮ  ቁጥር 06 ጥቅምት 5/2019 ዓ/ም በ3፡00 ይከፈታል፡፡
  9. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ በተገለፀበት ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ  ባሉት 5 ተከታታይ  ቀናት ውሥት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ ይኖርበታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን 20 በመቶ የመጨመርም የመቀነስም መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. መ/ቤቱ ጨረታውን በሚከፍትበት ቀን ብሄራዊ በዓል እና እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  12. ግብዓቱ የሚቀርበው በሙሉ ቢ/ወ/ግ/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ሲሆን በሙያተኛ ተረጋግጦ ገቢ ይሆናለ፡፡
  13. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር  058 254 06 04 /09 13 79 98 34 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የቢቡኝ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here