ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
85

በምስራቅ ጎጃም አስተዳደር ዞን የእነማይ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በስሩ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የህፃናት መገልገያ እቃዎች ከአልማ በጀት እና ለሴ/መ/ቤቶች ከመደበኛ በጀት የተለያዩ እቃዎችን ማለትም  ሎት 1. የደንብ ልብስ ብትን ጨርቃ ጨርቅ፣ ሎት 2. የደንብ ልብስ የተዘጋጁ፣ ሎት 3. የኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች፣ ሎት 4. የጽዳት እቃዎች እና የህፃናት መጫዎቻ አሻንጉሊት፣ ሎት 5. የቤት እና የቢሮ መገልገያ እቃዎች እና ሎት 6. የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-

  1. በዘርፉ አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ማያያዝ አለባቸው፡፡ ግዥው ብር 20,000 (ሃያ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ 3 በመቶ ታክስ የሚቆረጥ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ አለባቸው፡፡ የግዥው መጠን ብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ አሴት ታክስ (ቫት) የተመዝጋቢ ማረጋገጫ ሰርተፊኬ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ለእያንዳንዱ ሎቶች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ከሎት 1 እስከ ሎት 6 ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ ጨረታው  በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እነማይ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የፋይናንስ ቡድን ከገንዘብ ያዥ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት ማለትን ለሎት 1. ብር 6,000 (ስድስት ሽህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ)፣ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለበት፡፡ ለሎት 2. እና ለሎት 3 ብር 30,000 (ሰላሳ ሽህ ብር) ብቻ በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ)፣ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና አለበት፡፡ ለሎት 4፣5 እና ለሎት 6 ብር 10,000 (አስር ሽህ ብር) ብቻ በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ)፣ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለበት፡፡ ሆኖም ግን ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ከሆነ ገንዘቡን በመ/ቤታችን መሂ-1 ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
  5. ከሎት 1 እስከ ሎት 6 ላሉ ግዥዎች አሸናፊው አሸናፊነቱን ከተገለጸበት ቀን በኋላ ለውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ  ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለበት፡፡
  6. ከሎት 1 -6 አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን በእያንዳንዱ ሎት የገንዘብ መጠን ከብር 3,000,000 ( ሶስት ሚሊዮን ብር ) በላይ ከሆነ ውል በሚይዝበት ወቅት እ/ወ/ዐቃቢ ህግ የሚያስከፍለውን የአገልግሎት ክፍያ ሙሉ ወጭ መሸፈን አለበት፡፡
  7. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበረያ ለ72 ቀናት ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ለሁሉም ሎቶች ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ የሚውል ሲሆን በ11 ቀን ከረፋዱ 3፡30 ይታሸግና በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትብት ቀን ቅዳሜና፣ እሁድ እና የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ታሽጎ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡ በጨረታ ሰነዱ እና በፖስታው ላይ የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡
  9. በባለሙያ የሚረጋገጡ እቃዎች በባለሙያ እየተረጋገጡ የምንረከብ መሆኑ እና አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች በእነማይ ወረዳ ገ/አ/ል/ጽ/ቤት ሥር ባሉ ንብረት ክፍል ድረስ አስፈላጊውን ወጭ በመሸፈን ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
  10. በእያንዳንዱ ሎት መስሪያ ቤቱ አሸናፊ የሚለየው በጠቅላላ ዋጋ ጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ተጫራቾች በየሎት ምድቡ የቀረቡትን ሙሉ በሙሉ መሙላት አለባቸው፡፡ ዝርዝሩን ሙሉ በሙሉ ካልሞሉ ከጨረታ ውጭ (ውድቅ) ይሆናሉ፡፡
  11. ከሎት 1-6 ላሉ የሎት ምድቦች ጽ/ቤቱ የጨረታ አሸናፊ ከሆነው ተጫራች የጨረታ ይዘት ሳይቀይር ከእቃው ጠቅላላ መጠን ላይ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  12. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ አስፈላጊ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  13. ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ለ45 ቀናት ይሆናል፡፡
  14. የጨረታ መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ለውጥ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን  ማግልል አይችሉም፡፡
  15. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 665 01 00 /058 665 00 08 ደውሎ መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የእነማይ ወረዳ /ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here