የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት አመታዊ የሰራተኞች የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉና መወዳደር የሚችሉ ተወዳዳሪዎችን መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተወዳዳሪው የተሰማራበትን የንግድ ዘርፍ የሚያሳይ የታደሰና ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ፈቃዳቸውን ያሳደሱ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች የአንድ አመት የታክስ ክሊራንስ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ተወዳዳሪዎች ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን አግባብነት ያላቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
- የሚገዛው የደንብ ልብስ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ በቀረበው ሳምፕል መሰረት መሙላት አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 46 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ኢንቨሎፕ ሰነዶችን ለመለየት እንዲቻል በግልጽ ፅሁፍ በታሸገ ኢንቨሎፕ አድራሻን በመጥቀስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂው ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ይህ ማስታወቂያ በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 (ሃያ) ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ይቆያል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ን/አስ ቡድን ክፍል በቢሮ ቁጥር 46 በ21ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
- በዋጋ መሙያው የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጨረታ ውጭ ያስደርጋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 46 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 93 73 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ

