የመድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ደሴ ቅርንጫፍ በመ/ቤቱ እያገለገሉ ለሚገኙ የተለያዩ መጠን ያላቸውና የተለያዩ ሞዴል ያላቸውን የተለያዩ ተሸከርካሪዎችቻችንን IVECO፣ FSR ፣ ISUZU፣ ISUZU OBAMA፣ HUYUNDAI MID BUS፣ 1HZ፣ NISSAN PATROL፣ NISSAN PICK UP፣ COROLLA፣ መኪናዎችን ለ1 (አንድ) ዓመት የሚቆይ የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች (SPARE PART) ለመግዛት በዚህ ግልጽ ጨረታ በማውጣት ኮንትራት ውል ለዓመት ውለታ በመውሰድ እና በመያዝ የተሽከርካሪ እቃ አቅርቦቱን ማግኘት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን በመመሪያ ከፀደቀውና በላይ ከሆነ የተጨማሪ አሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ነገር ግን ከላይ ከ1-4 የተጠቀሱትን ያላቀረቡ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 25 (ሃያ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ጢጣ በሚገኘው በጠቅ/አገ/ንብ/አስተዳደር የሥራ ክፍል በአካል በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር)ብቻ በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከመክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) አንድ በመቶ በባንክ በተመሰከረለት (ሲፒኦ) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን ደረቅ ቸክ ማስያዝ አይቻልም፡፡
- በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 25 ከቀኑ 8፡00 ድረስ ለዚሁ ስራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ከቀኑ 8፡30 ተዘግቶ በዚሁ እለት ከቀኑ 9፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጢጣ በሚገኘው በመ/ቤቱ ቅጥር ግቢ ጥቅምት 13/2019 በይፋ ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የጨረታ ውድድሩን የሚያካሂደው በጠቅላላ ዋጋ ዝቅተኛ ዋጋ ባቀረበ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ቢፈልጉ ጢጣ በሚገኘው በጠቅ/አገ/ንብ/አስተዳደር የሥራ ክፍል በግንባር ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 033 115 05 53 /09 75 54 76 54 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኢትጵያ መድኃኒት አቅራቢ ድርጅት ደሴ ቅርንጫፍ

