ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
49

የመድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ደሴ ቅርንጫፍ በመ/ቤቱ እያገለገሉ ለሚገኙ የተለያዩ መጠን እና ሞዴል ያላቸውን የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን IVECO፣ FSR፣ ISUZU ፣ISUZU OBAMA፣ HUYUNDAI MID BUS፣ 1HZ ፣NISSAN PATROL፣ NISSAN PICK UP፣ COROLLA፣ መኪናዎች ለ1 (አንድ) ዓመት የሚቆይ የኮንትራት የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት ለማግኘት በግልጽ ጨረታ በማውጣት ኮንትራት ውል  በመያዝ የተሸከርካሪ ጥገና አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች  በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የግዥው መጠን በመመሪያ ከፀደቀውና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው ፡፡ ነገር ግን ከላይ ከ1-4 የተጠቀሱትን ያላቀረበ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 25 (ሃያ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ጢጣ በሚገኘው በጠቅ/አገ/ንብ/አስተዳደር የሥራ ክፍል በአካል በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከመክፈቻ  ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ሁለት በመቶ በባንክ በተመሰከረለት (ሲፒኦ) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን ደረቅ ቸክ ማስያዝ አይቻልም፡፡
  8. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  9. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 25 ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ድረስ ለዚሁ ስራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ከረፋዱ 3፡30 ተዘግቶ በዚሁ እለት ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጢጣ በሚገኘው በመ/ቤቱ ቅጥር ግቢ ጥቅምት 13/2019 በይፋ ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የጨረታ ውድድሩን የሚያካሂደው በጠቅላላ ዋጋ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ነው፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ቢፈልጉ ጢጣ በሚገኘው በጠቅ/አገ/ንብ/አስተዳደር የሥራ ክፍል በግንባር ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 033 115 05 53 መደወል ይችላሉ፡፡

 የኢትጵያ መድኃኒት አቅራቢ ድርጅት ደሴ ቅርንጫፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here