ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር 03/2019

0
34

የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የጥበቃ አውት ሶርስ (የአገልግሎት ግዥ) በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች ለመግዛት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ተወዳዳሪዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መስፈርት መሰረት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታ መወዳደር ይችላሉ፡፡

ተ.ቁ አገልግሎት የሚሰጥበት ፕሮጀክት(ቦታ) መለኪያ ብዛት ምርመራ
1 ለዙ-ሀሙሲት መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ለተለያዩ ፕሮጀክቶች በቁጥር 18  

 

  1. የዘመኑን ግብር ከፍለው በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የንግድ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እነዚህንና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ኮፒ በማድረግ በመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ማካተት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች በኮርፖሬሽኑ ስም የተሰራ (ሲፒኦ) ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል (un conditional bid bond guarantee) ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር 20,000 (ሃያ ሽህ ብር) ማስያዝ አለባቸው፡፡ አሸናፊው ከተለየና ውል ከተፈረመ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉ ድርጅቶች የጨረታ ማስከበሪያ ይመለስላቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 (ሃያ) ተከታታይ ቀናት በማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሽህ ብር) ብቻ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በዋጋ መሙያ ሰንጠረዥ ለተገለፀው የጥበቃ አውትሶርስ (የአገልግሎት ግዥ) የሚያቀርቡትን ማስረጃዎችና የሚሞሉትን ዋጋ አርጅናል እና ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ አይቻልም ካለ ግን ዋጋውን በሞላው አካል መፈረም ይኖርርበታል፡፡ በሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ላይ ህጋዊ የድርጅቱ ተወካይ ስምና ፊርማ እና ማህተም ያረፈበት መሆን ይኖርበታል፡፡
  6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ባሕር ዳር ከተማ በሚገኘው ዋና መ/ቤታችን ውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 25 በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  7. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡30 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሸያ ማድረግ አይችሉም፡፡
  8. ኮርሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ይህንንም በሚያደርግበት ጊዜ በኮርፖሬሽኑ የማስታወቂያ መለጠፊያ ቦርድ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 222 14 79 /09 30 11 1746 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here