ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ      የግዥ መለያ ቁጥር ግ/ጨ/004/2019

0
74

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ለአማራ ሞሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ህንፃ ለ2019 በጀት አመት አመታዊ የቢሮ ህንፃ እና ምድረ ግቢ የጽዳት አገልግሎት እና ኮስትር መኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ ግዥ አወዳድሮ አመታዊ ውል በመያዝ አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል፡፡የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት)ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. በግብር አመቱ ተገቢውን ታክስ እና የግብር ግዴታ የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ. 1 እስከ 4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የሚመለከታቸውን

ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

  1. የሚገዙ የአገልግሎት ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) ብቻ በመክፈል ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 315 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ማግኘት ወይም መግዛት ይቻላል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የመኪና ኪራይ 30,000 (ሰላሳ ሽህ ብር)፣ ለፅዳት አገልግሎት 15,000 (አስራ አምስት ሽህ ) ብር በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአብክመ ሲቪል ሰርቪስ የሰዉ ሃብት ልማት ቢሮ ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ሆኖ በ11ኛው ቀን እስከ 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 315 በ11ኛው ቀን 3፡30 ተዘግቶ በ4፡00  ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን  በ4፡00  ይከፈታል፡፡
  6. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉበሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  7. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 315 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 96 44/058 220 96 46 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት

ሲቪል ስርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ

ባህርዳር

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here