የአብክመ የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ለቢሮው፣ለፕላን ኢንስቲትዮት እና የከተሞች ምግብ ዋስትና እና ሴፍቲኔት ፕሮጀክት የተለያዩ እቃዎችን እና ተያያዥ አገልግሎቶችን ግዥ ለመፈፀም ስልጣን እና ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡በመሆኑም በቅርቡም ተሻሽሎ በወጣዉ የመንግስት የግዥ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 306/2018 የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 144/2018 መሰረት በማድረግ የ2019 ዓ/ም በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የመኪና ጎማ ከነካላማዳሪያዎች የተለያዩ የመኪና ታፒሰሪዎች(ዲኮር) እና አመታዊ የቢሮዎች፤ የመፀዳጃ ቤትና የግቢ የፅዳት አገልግሎት (አውትሶርስ) ግዥ በመደበኛ እና በፕሮጀከት በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅቶች ጋር ስምምነት በመያዝ ግዥውን መፈጸም ይፈልጋል ፡፡ሎት1. የተለያዩ የመኪና ጎማ ከነካላማዳሪያዎች ፣ሎት2. የተለያዩ የመኪና ዲኮር (የመኪና ታፒሰሪዎች) ሎት3. አመታዊ የቢሮ የመፀዳጃ ቤትና የገቢ የፅዳት አገልግሎት (አውትሶርስ) ግዥ በመደበኛ በጀት ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅቶች ጋር ውል በመያዝ በግልፅ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የንግድ ፈቃድ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
- ግዥው መጠን ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ) ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፒስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ) በመክፈል ከቢሮው ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 27 /28/ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫረቾች ህጋዊ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት1. የተለያዩ የመኪና ጎማ ከነካላማዳሪው ብር 40,000 (አርባ ሽህ)፤ ተጫራቾች ህጋዊ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና፣ ለሎት2. የመኪና ዲኮር (የመኪና ታፒሰሪዎች) ብር 3,000 (ሶስት ሽህ ብር) እና ተጫራቾች ህጋዊ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና፣ ለሎት3. አመታዊ የቢሮ፣የሽንት ቤትና የገቢ የፅዳት አገልግሎት (አውትሶርስ) ብር 5,000 (አምስት ሽህ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በቢሮው ገንዘብ ያዥ ገቢ በማድረግ ደረሰኝ ኮፒውን ከሰነዱ ጋር ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ በአንድ ፖስታ በከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 11፡30 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ በ11ኛው ቀን 3:30 ታሽጎ 4:00 ይከፈታል፡፡ ቅዳሜ፣ እሁድ እና የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤ ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ኃላፊነት የማይወሰድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 30 ድረስ በመገኘትወይም በስልክ ቁጥር 058 320 50 00/058 226 61 80 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ያለምንም ስርዝ ድልዝ
- የተሞላ ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ሰነዱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
አድራሻ፡- ሆምላንድ ሆቴል ፊት ለፊት
የአብክመ የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ

