የፍኖተ ሰላም ሆስፒታል 2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ አገልግሎቶች ማለትም ሎት 1. አጠቃላይ የግቢውን የጽዳት ሥራ ፣ ሎት 2. የጭነት አገልግሎት፣ ሎት 3. የተኝቶ ህክምና ምግብ አቅርቦት ግዥ እና ሎት 4. የግቢውን የጥበቃ ሥራ ግዥ ለመፈፀም በዘርፉ ፈቃድ የላቸው ነጋዴዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለ2019 በጀት ዓመት ውል በመያዝ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች በዝርዝር የቀረቡትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በውድድሩ ይችላሉ፡፡
- የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የጽዳት፣ የምግብ እና ጥበቃ አገገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የወቅቱን ግብር የከፈለሉበት ክሊራንስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የሚሰራውን የሥራ ዝርዝር መግለጫ (ስፔሰፊኬሽን) እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ግዥ ፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጽዳት እና የጥበቃ ተጫራቾች የሞሉትን የ 12 ወር ሂሳብ የጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ (በሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ጨረታውን ቢያሸንፉ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ (ሲፒኦ) ያሲዛሉ፣ የጭነት አቅራቢዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000 የውል ማስከበሪያ ብር 20,000 የተኝቶ ህክምና የበሰለ ምግብ አቅራቢዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 40,000 የውል ማስከበሪያ 100,000 ብር ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአማረኛ ቋንቋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሰረት በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም በየገፁ በማድረግና በፊርማ አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሆስፒታሉ ግዥ ፋይናንስ ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ ቀን ከዋለ በኋላ በ11 ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸግ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በጋዜጣ ከወጣበት በ11 ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸወ በተገኙበት በግዥ ፋይናንስ ቢሮ ክፍል ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት አይስተጓጎልም፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ (ማብራሪያ) ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 775 10 16 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ማሳሰቢያ ፡- አጠቃላይ የግቢውን የጽዳት ሥራ የሚወዳደሩ አገልግሎት ሰጭዎች አንድ ዓመት እና ከዚያ በላይ በመንግስት መስሪያ ቤት መስራታቸውን የሚያረጋግጥ ልምድ ማያያዝ አለባቸው፡፡
የፍኖተ ሰላም ሆስፒታል

