የኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውና ፍሳሽ ድርጅት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመቱ የሚያስፈልጉና ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1. ቧንቧና መገጣጠሚያ፣ ሎት 2. የጽህፈት መሳሪያ እና የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3. የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ሎት 4. የመካኒካል እቃዎች እንዲሁም ሎት 5. ኬሚካል እና ላብራቶሪ እቃዎች ስለዚህ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች መስፈርቶችን በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)፣ የዕቃ ወይም የአገልግሎት አቅራቢዎች የተመዘገቡ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙበትን ዕቃዎች የጠቀሜታ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚችሉ ሆኖ ናሙና ወይም ብሮሸር ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ሳምፕል ወይም ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ዘወትር በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 03 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን የቴክኒካሉን ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በሁለት ፖስታ ፋይናሽያሉን ሲፒኦውን ጨምሮ ኦርጅናል ኮፒ በማለት በሁለት ፖስታ ለየብቻ በመለየት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ተኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 05 በይፋ ይከፈታል፡፡ ሆኖም እለቱ የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የጨረታ ሰነዱን 4፡00 ድረስ በማስገባት ከረፋዱ 4፡30 በይፋ ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በድርጅቱ ስልክ ቁጥር 033 551 02 72 በመደወል ወይም በግንባር በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

