ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
49

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ የትራክተር መለዋወጫዎች፣ ጎማዎች እና ዘይትና ቅባት እና የዘር ማበጠሪያ ማሽን መለዋወጫ፣ የዘር ማሸጊያ ባዶ ጆንያ ህትመት ግዥ፣ ለብር ሸለቆ  ምርጥ ዘር ማባዣ ጣቢያ  የእንግዳ ማረፊያ፣የቀን ሠራተኛ ማደሪያ፣ እና እስቶር አገልግሎት የሚዉሉ የሸድ ግንባታ ደረጃ 5 ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ  እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማስገንባት እና በተጨማሪም የተለያዩ ለዘር የማይዉሉ ሰብሎች፣ብጣሪዎች፣ያገለገሉ ጆንያዎችን እና ያገለገሉ እቃዎችን ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የዘመኑን የመንግስት ግብር ስለመከፈሉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር (ቲን) እና ደረጃቸዉን የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግንባታዉ ጨረታ አሸናፊ ሁኖ የሚመረጠዉ በቴክኒካል መገምገሚያ መስፈርት እና በቀረበዉ ዝርዝር መሰረት በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበዉ ድርጅት ነዉ፡፡
  4. የማበጠሪያ ማሽን መለዋወጫ ለማቅረብ ፈቃድ የተሰጠዉና ከ2 ወር ባልበለጠ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለአንድ ሎት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) በአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ስም ማስያዝ አለባቸው።
  7. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፀው መሠረት የጨረታውን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ በማለት የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ትክክለኛ ስምና አድራሻ በመፃፍ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለግንባታዉ 21 ቀናት ፣ለዘር ማበጠሪያ ማሽን መለዋወጫ እስከ 15 ቀናት ሌሎች ጨረታዎች ለአስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ በሥራ ሰዓት በኢንተርኘራይዙ ዋና መስሪያ ቤት ባሕር ዳር ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  8. የግንባታዉ ሰነድ ኦርጅናሉ፣ኮፒዉ፣ቴክኒካሉ፣ፋይናንሻሉ እና የዋጋ ማሳወቂያዉ በተለያየ ፖስታ ሁኖ ሁሉንም ፖስታ አጠቃሎ በአንድ ፖስታ ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡ በእያንዳንዱ ፖስታ ምን ላይ ምን እንደያዘ መፃፍ አለበት፡፡
  9. ድርጅቶች ዋጋ ከሞሉበት ሰንጠረዥ ላይ እርጥብ ማህተም ወይም ፊርማ ማድረግ አለባቸው፡፡
  10. የተለያዩ ንፁህ ሰብሎች የምግብ እህሎች በተመለከተ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ናቸዉ፡፡
  11. ግዢዉን ባህር ዳር ዋናዉ መስሪያ ቤት መጋዘን መድሀኒዓለም አካባቢ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ሌሎች ዝርዝሩን ከጨረታ ሰነዱ ይመልከቱ፡፡
  12. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ በአለ በጅምላ ግቢ ዉስጥ በሚገኘዉ በአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ቢሮ 10ኛው ቀን በ8፡30 ይከፈታል፤ ቀኑ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል፡፡
  13. ኢንተርኘራይዙ ለግዥም ሆነ ለሽያጭ ከተጠየቀዉ ዉስጥ እንደአስፈላጊነቱ መጠን አስከ 50በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  14. ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ኢንተርፕራይዙ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 226 60 02 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 84 15/09 18 01 69 35 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here