የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች ባለው ክፍት የስራ መደብ ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታውን ከሚያሟሉ ስራ ፈላጊዎች መካከል በጊዜያዊ የረጅም ጊዜ (በኮንትራት)ቅጥር አወዳድሮ በመቅጠር ማሰራት ይፈልጋል፡፡
| ተቁ | የሥራ መደቡ መጠሪያ | ደረጃ | የመ/መ/ቁ | ደመወዝ | ብዛት | የሚሰራበት የሰራ ክፍል | የሥራ ቦታ | አማካኝ ውጤት (GPA)
|
ያጠናቀቁበት የትምህርት ዘመን | ተፈላጊ የትምህርት ዝግጅት | ተፈላጊ የስራ ልምድ |
| 1 | የህግ ባለሙያ 1 | 8 | አሚ-14 | በኮርፖሬሽኑ የደመወዝ ስኬል መሠረት | 01 | የህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት | ባሕር ዳር | ለወንዶች 3.00 ነጥብ እና በላይ
ለሴቶች 2.75 እና በላይ |
2018 ዓ.ም የተመረቁ ብቻ | በህግ የትምህርት መስክ የሰለጠነ | · በህግ የመጀመሪያ
ዲግሪና 0 ዓመት የስራ ልምድ |
ማሳሰቢያ፡-
- የምዝገባ ቀን በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆናል፡፡
- አመልካቾች ለፈተና በሚቀርቡበት ጊዜ ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አመልካቾች በእምነት ማጉደል በማጭበርበር ወይም በስርቆት ወንጀል ተከሰዉ ስልጣን ባለዉ አካል ተፈርዶባቸዉ የመቀጠር መብታቸዉን እንዲጠቀሙ ስልጣን ያለዉ ፍርድ ቤት የወሰነበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አመልካቾች ለፈተና በሚቀርቡበት ጊዜ ኦርጅናሉን የትምህርት ማስረጃ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከተጠቀሰዉ አግባብነት ያለው የትምህርት ዝግጅት ውጭ ለምዝገባ የሚቀርቡ ሌሎች ማስረጃዎች ተቀባይነት አይኖራቸዉም፡፡
- መልካም ስነ-ምግባር ያለው/ላት፣ ከማንኛውም ደባል ሱስ የፀዳ/ች፣ ጥሩ ስብዕና ያለው/ላት፡፡
- በተመዘገቡበት የስራ መደብ ለምን ተቀጥረው መስራት እንደፈለጉ በጽሁፍ ገልፀው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አመልካቾች የሙያ ብቃት በሚያስፈልጋቸው የትምህር ዝግጅት የብቃት ማረጋገጫ በማስታወቂያው በተጠየቀው የትምህርት ደረጃ ልክ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በዚህ ማስታወቂያ ተወዳድሮ ያለፈ ከወንጀል ነፃ መሆኑን ከሚኖሩበት ቀበሌ አስተዳደር ወይም የህግ አካላት ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
- በተጠቀሰው የትምህርት መስክ የሙያ ብቃት ምዘና የማይሰጥ ከሆነ ከሚመለከተው ተቋም የሙያ ብቃት አለመጀመሩን ማስረጃ ካቀረቡ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
- የኮንትራት ቅጥሩ ለ6 ወር ሆኖ እንደአስፈላጊነቱ በየ6 ወሩ ይታደሳል፡፡
- ፈተና የሚሰጥበት ቀንና ቦታ በሌላ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡
- በጽኑ እስራት በሚያስቀጣ ወንጀል ተከሶ የተፈረደበትና ከእስር የተፈታ እንዲሁም በዲሲፕሊን ጉድለት ምክንያት ከስራ የተሰናበተ በኮርፖሬሽኑ ሊቀጠሩ አይችሉም፡፡
- አመልካቾች የምትመዘገቡበት ሊንክ በዌብሳይታችን ameco.etማግኘት ትችላላችሁ ወይም ይህ ሊንክ በመጫን ይመዝገቡ https://forms.gle/51Ppw7W28sk8rvTv5 መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን እናሳስባለን፣
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 226 50 07 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
ባሕር ዳር

