ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
58

የምዕ/ጎጃም ዞንና አካባቢው አልማ ልማት ጽ/ቤት በራስ አቅም የመልማት ምልክት የሚል መርህ አንግቦ በክልላችን ተመስርቶ አየሰራ ያለ መሆኑ ይታዎቃል፡፡ በመሆኑም በዞኑ ስር ለሚገኙ የወረዳ አልማ ልማት ጽ/ቤቶች ስራ ግብዓት አገልግሎት የሚውሉ የፈርኒቸር እና ላፕቶፕ ኮምፒውተር፣ የተማሪዎች ዩኒፎርም፣ ደብተር ፣እስክርቢቶ እና የተማሪዎች ቦርሳ ግዢ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር (ቲን)፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ ደረሰኝ ተመዝጋቢ የሆኑ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያያዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 500 (አምስት መቶ) ብር በመክፈል ምዕ/ጎጃም/ዞንና አካ/አልማ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የመጨረቻ ሰነድ ሲያቀርቡ የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ዋጋ ሲፒዮ አንድ በመቶ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች መሰረት በማድረግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ ይቆያል፣ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በምዕ/ጎጃም/ዞንና አካ/አልማ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው በ 16 ኛው ቀን  4:00 ላይ ይታሸጋል፣ በዚሁ ቀን  4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ተጫራቾች ባይገኙ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡
  6. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመገኘት መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. አሸናፊው ድርጅት ለሚያቀርበው ዕቃ ጽ/ቤቱ ቢሮ ድረስ በመቅረብ የውል ማስከበሪያ ሲፒዮ የጠቅላላ ዋጋውን 10በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም ይኖርበታል፡፡
  8. የዕቃውን ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ሽያጭ ጋር ማግኘት ይቻላል፡፡
  9. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ሲያስገቡ የተወዳዳሪው ማህተም የተደረገበት የዕቃ ስፔስፊኬሽን አብረው ማስገባት ይጠበቃባቸዋል፣ይህ ካልሆነ ከጨረታ ውድድር ውጭ ያደርጋሉ፡፡
  10. የጨረታ አሸናፊው እንደ አስፈላጊነቱ በነጠላ ወይም በድምር ዋጋ የሚለይ ይሆናል፡፡
  11. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

    የምዕ/ጎጃም ዞንና አካባቢው አልማ ልማት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here