ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
48

በአብክመ በሰሜን ጎንደር ዞን በጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1.የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ሎት ፣ 2.የመኪና ጎማ እና ባትሪ ፣ ሎት 3.የመኪና የሞተር ዘይት እና የጥርሳ ጥርስ ዘይት  በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ጽ/ቤቱ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

  1. በዘመኑ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ አለባቸዉ ፡፡
  2. የግብር ከፋይ(ቲን)ሰርቲፍኬት ማያያዝ አለባቸዉ፡፡
  3. ተጫራቾች የዘመኑ ግብር የከፈሉበት የግብር ክሪላንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  4. የተጨማሪ ሴት ታክስ የምዝገባ ሰርቲፍኬት ፎቶ ኮፒ ማያያዝ አለባቸዉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. በእያንዳንዱ ሎት የዕቃወቹን አይነትና ዝርዝር መገለጫ (ስፔስፍኬሽን )ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300(ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2 በመቶ በእያንዳንዱ ሎት ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ፣ቢድ ቦንድ ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመ/ሂ-1 (አንድ ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣ ከጥቅምት 02/2019 ዓ/ም እስከ ጥቅምት 11/2019 ዓ/ም ድረስ ይቆያል፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ቀናት ከጥቅምት 02/2019 ዓ/ም እስከ ጥቅምት 11/2019 ድረስ ማስገባት ይቻላል፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 10 በቀን ጥቅምት 12/2019 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡15 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም የጨረታ ከፈታ ስርዓቱን አያስተጓጉለውም፡፡
  12. ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር (በሎት) ድምር ይሆናል፡፡
  13. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ሊኖረው አይፈቀድም ካለውም ወድቅ ይሆናል፡፡
  14. ተጫራቶች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም፤ ስምና ፊርማ ማድረግ አለባቸው፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. የእቃዎቹ ርክክብ የሚፈጸመው ጥራታቸው በባለሙያ ሲረጋገጥ ነው ፡፡
  17. ተጫራቾች የመኪና መለዋወጫ የእቃዎቹ ርክክብ የሚፈጸመዉ ማ/ጎ/ዞን ከሻጭ መጋዝን ሲሆን ሌሎች እቃዎች ማለትም .የመኪና ጎማ ፣ ባትሪ፣ የመኪና የሞተር ዘይት እና የጥርሳ ጥርስ ዘይት ጃ/ወ መ/ብርሃን ንብረት ክፍል ሲሆን ተጫራቾች ማውረጃና መጫኛ አስበው መሙላት አለባቸው ፡፡
  18. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ.10 በአካል በመገኘት ወይም በስቁ. 0582940023 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here