ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
58

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ያገለገሉ  ዕቃዎችን  በግልጽ ጨረታ ዘዴ በጋዜጣ ተጫራቾችን አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት መሸጥ ይፈለጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታዉ ለመወዳደር የሚፈለጉ ዉድቅዳቂዎች እና እስክራፕ ዉጤቶች ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ ድርጅቶች ፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፍኬት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጠቅላላ ድምር ዋጋ ብር 200,000(ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15(አስራ አምስት/) ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 106 ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይቻላል፡፡ ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነዶችን በጥንቃቄ በፖስታ ለየብቻ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
  4. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥ ክፍል 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ(ስፒኦ)፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው የሚከፈትበት 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡3ዐ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  7. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. የሚሸጡትን ዕቃዎች ዓይነት፣ ብዛትና ስፔስፍኬሽን እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደዉ አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ድረስ በመምጣት መዉሰድ ይቻላል፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

ባህር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here