ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
6

የአብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት ዋና መ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ህጋዊና ብቃት ካላቸው በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2. የፅዳት እቃዎች፣ ሎት 3. የደንብ ልብስ ግዥ፣ ሎት4. ሸሚዝና ተዛማጅ የደንብ ልብሶች፣ ሎት 5. የመኪና ጎማ እና ተዛማጅ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የአብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት ዋና መ/ቤት አድራሻው ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 03 ባህር ዳር ጤና ጣቢያ ፊት ለፊት በስተ ሰሜን በኩል ሁለተኛ ብሎክ ባለዉ G+3 ህንጻ ላይ ቢሮ ቁጥር 305 በመምጣት የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ )  በመክፈል በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  1. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ የስራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒዬ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባችኋል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ የስራ ቀናት በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  5. ድርጅቱ ከአሸናፊው ድርጅት ንብረቱን የሚረከበው በተጠቃሚዎች የጥራት ትክክለኛነት ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡
  6. አሸናፊው ለአሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10 በመቶ የዉል አፈጻጸም ዋስትና (ፐርፎርማንስ ቦንድ በባንክ በተረጋገጠ  (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱም ሆነ ከተጠየቀዉ እስፔስፊኬሽን ዉጭ ምንም አይነት ፅሁፍ ማስፈር የለባቸውም፡፡
  8. ከጨረታ ሳጥን መዝጊያ ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ22ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሠዓት ተዘግቶ በዕለቱ በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 203 ከቀኑ 4፡15 በግልጽ ይከፈታል፡፡ በ22ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡ ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0900862330 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
    አብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here