በማሌዥያ ከዋና ከተማዋ ኳላላምፑር በስተሰሜን 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሁለት ግዙፍ ህንፃዎች ተገንብቶ 7,351 አገልግሎት መስጫ ክፍሎች ያሉት የዓለማችን ትልቁ ሆቴል ሊሆን መቻሉን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ አስነብቧል::
ሆቴሉ በተሰጠው ባለሦስት ኮከብ ደረጃው ሳይሆን ቀዳሚነቱን ያገኘው፤ በመገልገያ ክፍሎቹ ብዛት መሆኑ ተገልጿል። ሆቴሉ 3,164 መደበኛ፣2,922 ጥንድ፣ 649 ባለ ሦስት ኮከብ ቅንጡ፣480 ልእለ ቅንጡ እና “ወርልድ ክለብ ሩምስ” አሉት::
በ “ጀንቲንግ” ቡድን የተገነባው ሆቴሉ ከደቡብ እስያ ሀገራት ለሚጐርፉ ቱሪስቶች መገናኛ ማእከል መሆኑም ተጠቁሟል።
ሆቴሉ በሁለተኛ ደረጃ ከሚከተለው የላስቬጋሱ ቬኒቲያን ሆቴል በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት በደንበኞች ሙሉ በሙሉ በመያዙ ተበልጦ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ግን 90 በመቶ ክፍሎቹ በተገልጋዮች እየተያዙ ነው።
ለሆቴሉ ከዓለም በትልቀነቱ ቀዳሚ መሆን ለጉብኝት መዳረሻ፣ ለገበያ ማእከል ያለው ቅርበት ተመራጭ አድርጐታል::
(ታምራት ሲሳይ)
በኲር የሚያዚያ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም


