የሰቲት ሁመራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ፡- 1. የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች፣ 2. ልዮ ልዩ የጽህፈት መሳሪያ፣ 3. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ 4. የጽዳት ዕቃዎች፣ 5. የባህላዊ ሙዚቃ መሳሪያዎችና አልባሳት ዕቃዎች እንዲሁም 6. የሰፖርት ቁሳቁስ እቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ፡-
- በዘርፉ የሚመለከተው የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ሰቲት ሁመራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 15 በመምጣት የተሟላ የጨረታውን ዝርዝር ማስታወቂያና ሙሉ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን በጨረታ ማስታወቂያው ላይ በተጠቀሰው ቦታ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 79 46 41 82 /09 18 75 30 64 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሰቲት ሁመራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

