ልጅ ለአባቱ

0
14

አውስትራሊያዊው ቻርለስ ስሚዝ በ91 ዓመታቸው ሲያልሙት የኖረ ፍላጎታቸው ተሳክቶ በአዛውንትነት እድሜያቸው ለአያትነት የበቁ አንጋፋ መሆናቸው ተረጋግጦ ለክብረወሰን መብቃታቸውን የፒአይ ድረ ገጽ ሰሞኑን አስነብቧል::

የዓለም ድንቃድንቅ መዝጋቢ ድርጅት እንዳስታወቀው አዛውንቱ ቻርለስ ስሚዝ በ91 ዓመት ከ209 ቀናት እድሜያቸው ከልጃቸው አሽሊ ስሚዝ እና ከልጃቸው ሚስት ሀና  ሴት ልጅ በመወለዷ በከፍተኛ የእድሜ ጣሪያ ለአያትነት የበቁ አዛውንት ሆነው ለክብረ ወሰን በቅተዋል::

የአዛውንቱ ቻርለስ ስሚዝ ልጅ አሽሊ ስሚዝ በ55 ዓመቱ ከባለቤቱ ሀና ቶሎ ተጋብቶ ልጅ ለመተካት ሦስት ጉልቻ መመስረታቸውን ተናግሯል:: የጥንዶቹ ጥምረት ሰምሮም ለአንጋፋ አያትነት ክብር አብቅተዋቸዋል::

አሽሊ ስሚዝ የአባቱን ለአያትነት የመብቃት ህልም ከማሳካቱ ባሻገር በድንቃድንቅ መዝገብም ባለክብረወሰን መሆናቸውን ነው በእማኝነት ያረጋገጠው ::

ከአባቱ አስደናቂ ባህሪያት አንዱ እና ዋነኛው ነፃነታቸው መሆኑን ያወሳው ልጃቸው አሽሊ ስሚዝ አባቱ ጡረታ ከወጡ ጀምሮ በአውስትራሊያ በተለያዩ ቀጣናዎች በተሽከርካሪ እና በጀልባ በመጓጓዝ እየተዝናኑ እንደሚያሳልፉም ነው የተናገረው:: አሽሊ ስሚዝ እርጅና አባቱን ከምንም ነገር እንዳላገዳቸው ነው አፅንኦት ሰጥቶ ያስረዳው:: በዚህም አሁን ባሉበት የእድሜ ጣሪያ ላይ ሆነውም ንቁ መሆናቸውን ነው  የገለፀው::

አዛውንቱ አባቱ ለብዙ ነገሮች አዎንታዊ አመለካከት ያላቸው መሆናቸው እና ጠንካራ መሰሎቻቸው በተሰባሰቡበት የአዛውንቶች ክበብ አባል መሆናቸው የንቁነታቸው መሰረት መሆኑን በማብሰር አጠቃሏል-አሽሊ ስሚዝ::

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሚያዚያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here