ለክብረወሰን የበቁት በጐ ፈቃደኞች

0
14

በአሜሪካ የ “ሚልዋውኪ ሪቨር ኪ “ፐር የተሰኘ የበጐ ፈቃደኞች ማህበር ከትሩ ኧርዝ” የፅዳት እቃዎች አቅራቢ ኩባንያ ጋር በመተባበር በወንዝ ፅዳት ላይ ባሰማራቸው 2082 አባላቱ ብዛት በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝጋቢ ድርጅት ክብረወሰን ሆኖ መመዝገቡን ዩፒአይ ድረ ገጽ ሰሞኑን አስነብቧል፡፡

 

ከሳምንት በፊት የበጐ ፈቃደኞች ማህበሩ ባካሄደው 31ኛው አመታዊ የፅዳት መርሃ ግብር በተለያየ የእድሜ ክልል የሚገኙ አባላቱን ከ120 የወንዝ ዳርቻ ቦታዎች  በማሰማራት ቆሻሻዎችን ማስወገድ ችለዋል፡፡

በጐ ፈቃደኞቹ በፅዳት መርሀ ግብሩ ከ100,000 ፓውንድ በላይ ቆሻሻ መሰብሰባቸውም ተጠቁሟል፡፡

 

የበጐ ፈቃደኞች ማህበሩ ዋና ዳይሬክተር ጄኒፈር ቦልገር ብሬሴዳ ለክብረ ወሰን የበቁት ሰዎች ስለወንዞች ጠቀሜታ ጥልቅ  ግንዛቤ በማዳበራቸው መነሻ መሆኑን አስምረውበታል፡፡ ለዚህም ከበጐ ፈቃደኞች ማህበሩ ጋር በጥምረት ለሰሩ ድርጅቶች የላቀ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

 

ለ “ሚልዋውኪ ሪቨርኪፐር” በጐፈቃደኞች የፅዳት ስራ አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎች በማድረግ የተባበረው ትሩ ኧርዝ የፅዳት አቅራቢ ኩባንያ ዋና ስራአስኪያጅ ብራድሊስኪ የበጐ ፈቀደኞቹን አርዓያነት ያለው ተግባር በመደገፋቸው ክብር እንደሚሰማቸው ነው ያረጋገጡት፡፡

ብራድ ሊስኪ ከበጐ ፈቃደኞች ማህበሩ ጋር በጋራ በመስራታቸው የተገኘው ክብወረሰን  የትልቅ ክብር ተጋሪ እንዳደረጋቸው ነው ያስረዱት፡፡

 

በመጨረሻም ከበጐ ፈቃደኞች ማህበሩ ጋር የሰራው ትሩ ኧርዝ ሌሎች ኩባንያዎችም ለትርፍ ካልተቋቋሙ በጐ ፈቀደኞች ጋር በመተባበር ለውጥ ማምጣት እንደሚችሉ በመግለጽ ቅንጅታዊ ስራዎችን አጠናክረው መቀጠል እንደሚኖርባቸው ጥሪ አቀርቧል፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here