ማስያስ የቁም እንስሳት እርባታ ኃ/የተ/የግል ማህበር በሰሜን ሸዋ ዞን በደብረ ብርሃን ከተማ ጠባሴ ክ/ከተማ 07 ቀበሌ ልዩ ቦታው ገነት ተብሎ በሚጠራው ቦታ የጥቁር ድንጋይ ማዕድን ማምረት ሥራ ፈቃድ እንዲሰጣቸው መሥሪያ ቤታችንን ጠይቀዋል፡፡
የጂኦግራፊክ ኮኦርዲኔቶችም፡-
Adindan UTM Zone 37N
Geographic Coordinates of the license area
Block 1፡-
| id | X | Y |
| 1 | 551456.1644 | 1069997.2501 |
| 2 | 551585.8845 | 1070045.2635 |
| 3 | 551861.4533 | 1070097.3750 |
| 4 | 551855.6819 | 1070175.6124 |
| 5 | 551605.0003 | 1070150.9986 |
| 6 | 551569.9334 | 1070225.5165 |
| 7 | 551456.9875 | 1070199.5153 |
አዋሳኝ ቦታዎች
| በሰሜን | በደቡብ | በምዕራብ | በምሥራቅ |
| ሽመልስና ቄስ ተ/ፃዲቅ | መንገድ | እቴነሽ ሸዋታጠቅና ጥላሁን | መንበር አውሌ |
ስለዚህ የተጠየቀውን ፈቃድ ከመስጠታችን በፊት በተጠቀሰው አካባቢ በተለይም ከዚህ በላይ በተመለከቱት የጂኦግራፊክ ኮኦርዲኔቶች በሚከለል ቦታ ላይ ይገባኛል የሚል ካለ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሰባት /07/ ቀናት ውስጥ ተቃውሞውን በጽሑፍ ለመሥሪያ ቤታችን እንዲያቀርብ እናሳስባለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 222 12 37/21 42 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአብክመ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ

