ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ ቋሚ ቅጥር ማስታወቂያ

0
8

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች ያሉትን ክፍት የስራ መደቦች ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታውን ከሚያሟሉ ስራ ፈላጊዎች መካከል በቋሚ ቅጥር

አወዳድሮ በመቅጠር ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ተቁ የሥራ መደቡ መጠሪያ ደረጃ የመ/መ/ቁ ደመወዝ ብዛት ዳይሬክቶሬት/ዝግጅት የሥራ ቦታ ተፈላጊ የትምህርት ዝግጅት ተፈላጊ የስራ ልምድ
1. አረብኛ ቋንቋ ከፍተኛ ሪፖርተር 2

 

12 አሚ-1525

 

በኮርፖሬሽኑ የደመወዝ ስኬል መሠረት 01 አዲስ አበባ ኅብር ዝግጅት አዲስ አበባ በብሮድካስት ጋዜጠኝነት ፣በጋዜጠኝነትና ተግባቦት፣(ኮሞኒኬሽን)፣ ስነጽሁፍ ፣በቋንቋ፣ፖለቲካል  ሳይንስ  ዓለም  አቀፍ ግንኙነትና በተዛማጅ  የትምህርት  መሰክ የሰለጠነ የመጀመሪያ ድግሪና 3 ዓመት ወይም ሁለተኛ ዲግሪና 1 ዓመት  አግባብነት ያለው የስራ ልምድ ከአማርኛ በተጨማሪ የአረብኛ ቋንቋ መስማት፣መናገር ፣ማንበብና መጻፍ የሚችል፡፡

 

2. አፋርኛ ቋንቋ ከፍተኛ ሪፖርተር 2 12 አሚ-1500 በኮርፖሬሽኑ የደመወዝ ስኬል መሠረት 01 አዲስ አበባ ኅብር ዝግጅት አዲስ አበባ በብሮድካስት ጋዜጠኝነት ፣በጋዜጠኝነትና ተግባቦት፣ተግባቦት(ኮሞኒኬሽን)፣ ስነጽሁፍ ፣በቋንቋ፣ፖለቲካል ሳይንስ ዓለም አቀፍ ግንኙነትና በተዛማጅ የትምህርት መሰክ የሰለጠኑ፡፡ የመጀመሪያ ድግሪና 3 ዓመት ወይም ሁለተኛ ዲግሪና 1 ዓመት  አግባብነት ያለው የስራ ልምድ ከአማርኛ በተጨማሪ አፋርኛ  ቋንቋ መስማት፣መናገር ፣ማንበብና መጻፍ የሚችሉ፡፡

 

 

ማሳሰቢያ፡-

  • የምዝገባ ቀን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን  ጀምሮ ለ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል፡፡
  • አመልካቾች ለፈተና በሚቀርቡበት ጊዜ ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ፣ የትምህርት ማስረጃቸውን ኦርጅናል ከማይመለስ ኮፒ ጋር ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • አመልካቾች በእምነት ማጉደል በማጭበርበር ወይም በስርቆት ወንጀል ተከሰዉ ከሆነ ስልጣን ባለዉ አካል ተፈርዶባቸዉ የመቀጠር መብታቸዉን እንዲጠቀሙ ስልጣን ያለዉ ፍርድ ቤት የወሰነበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ከተጠቀሰዉ አግባብነት ያለው የትምህርት ዝግጅት ውጭ ለምዝገባ የሚቀርቡ ሌሎች ማስረጃዎች ተቀባይነት አይኖራቸዉም፡፡
  • አመልካቾች መልካም ስነ-ምግባር ያላቸው፣ ከማንኛውም ደባል ሱስ የፀዱ፣ጥሩ ስብዕና ያላቸው፡፡
  • ተወዳዳሪዎች በተመዘገቡበት የስራ መደብ ለምን ተቀጥረው መስራት እንደፈለጉ በጽሁፍ ገልፀው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • አመልካቾች የሙያ ብቃት በሚያስፈልጋቸው የት/ት ዝግጅት የብቃት ማረጋገጫ በማስታወቂያው በተጠየቀው የት/ት ደረጃ ልክ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • የሙያ ብቃት ምዘና ያልተጀመረባቸው የትምህርት መስኮች ከሚመለከተው ተቋም የሙያ ብቃት አለመጀመሩን ማስረጃ ካቀረቡ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
  • በግል የተሰራባቸው የሰራ ልምዶች የሰራ ግብር የተከፈለበት ማስረጃ ከገቢዎች ጽ/ቤት ማቅረብ ይገባል፡፡
  • ከአንድ የስራ መደብ በላይ መመዝገብ አይቻልም፡፡
  • የፈተና ቦታና ፈተና የሚሰጥበት ቀን በሌላ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡
  • አመልካቾች የምትመዘገቡበት ሊንክ በዌብሳይታችን amharaweb.com ማግኘት ትችላላችሁ ወይም https://forms.gle/WduRr5oxMNHw6JHn7 መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
  • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 226 5007 ይደዉሉ፡፡

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

ባህር ዳር

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here