የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
8

በምዕራብ ጎጃም ዞን የፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት ለ3ኛ ጊዜ  የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት ለመኖሪያ እና ለሆቴል አገልግሎት የሚውሉ የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ለመጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ግለሰብ ከሰኔ 09/2018 ዓ.ም ጀምሮ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ ለመኖሪያ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ለሆቴል ብር 400 (አራት መቶ ብር) የማይመለስ በመክፈል እና የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) 35 በመቶ በማስያዝ በከተማ አስተዳደሩ ቅጥር ግቢ ቢሮ ቁጥር 76 ድረስ በመምጣት ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

  1. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ከሰኔ 09/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 22/2018 ዓ/ም 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
  2. ጨረታው የሚዘጋው ሰኔ 22/2018 ዓ.ም በ11፡00 ይሆናል፡፡
  3. ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጸው መርሀ-ግብር መሰረት ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው የሚከፈተው ሰኔ 23/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 በከተማ አስተዳደሩ ቅጥር ግቢ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
  5. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  6. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በስልክ ቁጥር 058 775 08 13 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here