ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
10

የግዥ መለያ ቁጥር መ/ግ/001/2018 ዓ.ም

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃበት ልማት ቢሮ እና ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ለ2019 በጀት አመት አመታዊ የህንፃና ምድረ ግቢ የጽዳት አገልግሎት እና የተሸከርካሪ መለዋወጫ እቃ አቅርቦት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ

ውል በመያዝ ማስፀዳትና መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለዕቃዎች ግዥ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 007 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ማግኘት ወይም መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ለመኪና የዕቃ ግዥ ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ እንዲሁም ለጽዳት አገልግሎት ብር 10,000 (አስር ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአብክመ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት  ልማት ቢሮ ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው  በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት እስከ 3፡30  ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 007 በ16ኛው ቀን 3፡30 ተዘግቶ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 007 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም  በስልክ ቁጥር 058 220 96 44 /058 220 96 46 በመደወል መረጃ ማግኜት ይችላሉ፡፡

የአብክመ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ/ፑል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here