የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
17

በአመልካች/ከሳሽ የሽወርቅ ጌጡ እና ተጠሪ/ተከሳሽ ዮሀንስ ጌትነት መካከል ስላለው የባልና ሚስት ክርክር ጉዳይ  በየሽወርቅ ጌጤ ስም በባሕር ዳር ከተማ ማራኪ ቀበሌ በምሥራቅ ባዶ ቦታ፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን ባዶ ቦታ  እንዲሁም በደቡብ ባዶ ቦታ የሚያዋስነውን G+3 መኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 7,643,428  (ሰባት ሚሊዮን ስድስት መቶ አርባ ሶስት ሺህ አራት መቶ ሃያ ስምንት ብር) ሰኔ 23/2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 22/2018 ዓም በጋዜጣ በማዋል በጨረታ ይሸጣል፡፡ ስለሆነም መጫረት የምትፈልጉ ሁሉ የጨረታ መነሻ ዋጋውን በመያዝ ከጨረታው ቦታ በመገኘት መጫረት የምትችሉ ሲሆን የጨረታው ቀንም ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 7፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ ይካሄዳል፡፡ ስለዚህ መጫረት የምትፈልጉ ሁሉ ከላይ በተገለፀው ቀንና ሰዓት ንብረቱ ባለበት ቦታ ባሕር ዳር ከተማ ማራኪ ቀበሌ ድረስ በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- ቤትና ቦታው በሊዝ የተገዛና የሊዝ ቀጣይነት ያለው ክፍያ መክፈል የሚችሉ መሆን አለበት

የባሕር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here