በድጋሜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
42

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳድር ዞን የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት የሲቲስካን ክፍል የሪኖቬሽን ስራ ደረጃ 6 እና በላይ የሆኑ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

  1. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥ (ቲን) ካርድ ሰርተፊኬት እና ከመንግስት የሚጠበቅባቸዉን የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸዉ ማስረጃ የግብር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥዉ መጠኑ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  5. ስለጨረታው አጠቃላይ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 3 መዉሰድ የሚቻል ሲሆን ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት   ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛዉ ቀን ድረስ እስከ 11፡30 ብቻ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በልዩ ልዩ ምክንያት በሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ያልታገዱ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸዉን በአማርኛ ቋንቋ ማንኛውንም የመንግስት ግብር ያካተተ ሆኖ የጨረታ ሰነዱ በፖስታ ታሽጎ የድርጅቱ ክብ ማህተም፣ ፊርማ እና አድራሻ ማስቀመጥ አለባቸዉ፡፡ በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ማድረግ የለባቸዉም፡፡ የጨረታ ሰነዱን ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ማንኛዉንም የመንግስት ግብር አካቶ የሞሉትን ጠቅላላ ድምር አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሆስፒታሉ የጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ  ገቢ በማድረግ ከፖስታው ውስጥ አብሮ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
  9. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸዉ ከታወቀ ማንኛዉንም የመንግስት ግብር አካቶ የሞሉትን ጠቅላላ ድምር 10 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሆስፒታሉ የጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  10. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆይና በ16ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ባይገኙም ፕሮግራሙ የማይስተጓጎል ይሆናል፡፡
  11. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የመንግስት የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  12. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 827 04 27 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here