ጊዚያዊ የረጅም ጊዜ ኮንትራት ቅጥር  ማስታወቂያ

0
29

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን  በአዲስ አበባ ቅርንጫፍ    ከዚህ በታች በተጠቀሰው  ክፍት የስራ መደብ አስፈላጊዉን የትምህርት ዝግጅትና የስራ ልምድ ተፈላጊ ችሎታውን ከሚያሟሉ  ስራ ፈላጊዎች መካከል ጊዚያዊ የረጅም ጊዜ /በኮንትራት / ቅጥር አወዳድሮ በመቅጠር ማሰራት ይፈልጋል፡፡

 

ተቁ የሥራ መደቡ መጠሪያ ደረጃ የመ/መ/ቁ ደመወዝ ብዛት ዳይሬክቶሬት የሥራ ቦታ አግባብ ያለው የትምህርት ዝግጅት አግባብ ያለው የስራ ልምድ
1 የድምጽ ባለሙያ /ኦዲዮ ኢንጅነር 1/ 10 አሚ-1611 በኮርፖሬሽኑ የደመወዝ ስኬል መሰረት 01 አዲስ አበባ ሚዲያ ቴክኖሎጂ አዲስ አበባ በኤሌክትሪካል፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮምፒውተርና ኤሌክትሮ ሜካኒካል፣ በብሮድካት ምህንድስና እንዲሁም በመረጃና ኮሙንኬሽን ቴክኖሎጂ፣ በኤሌክትሮኒክስና ተግባቦት ቴክኖሎጂ፣ በኤሌክትሮኒክስ ተግባቦት ቴክኖሎጂ ስራ አመራር፣ ሲኒማቶግራፊ ፣ቪዲዮግራፊ ፣ ብሮድካስት ጋዜጠኝነት፣ ኦዲዮቪዲዮ ቴክኖሎጂ፣ ፎቶ ኢሜጅንግ፣ አርት ፔይንቲግ ወይም በተዛማጅ የትምህርት መስክ የሰለጠነ የመጀመሪያ ዲግሪና 2 ዓመት አግባብነት ያለው የስራ ልምድ

ማሳሰቢያ፡-

  • የምዝገባ ቀን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን  ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆናል፡፡
  • አመልካቾች ለፈተና በሚቀርቡበት ጊዜ ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • አመልካቾች በእምነት ማጉደል በማጭበርበር ወይም በስርቆት ወንጀል ተከሰዉ ስልጣን ባለዉ አካል ተፈርዶባቸዉ የመቀጠር መብታቸዉን እንዲጠቀሙ ስልጣን ያለዉ ፍርድ ቤት የወሰነበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • አመልካቾች ለፈተና በሚቀርቡበት ጊዜ ኦርጅናሉን የትምህርትና የስራ ልምድ ለተጠየቀበት መደብ ብቻ የስራ ልምዳቸውን መረጃ ኦርጅናል ይዘዉ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ከተጠቀሰዉ አግባብነት ያለው የትምህርት ዝግጅት እና የሥራ ልምድ ውጭ ለምዝገባ የሚቀርቡ ሌሎች ማስረጃዎች ተቀባይነት አይኖራቸዉም፡፡
  • አመልካቾች መልካም ስነ-ምግባር ያለው/ላት ከማንኛውም ደባል ሱስ የፀዳ/ች እና ጥሩ ስብዕና ያለው/ላት፡፡
  • ተወዳዳሪዎች በተመዘገቡበት የስራ መደብ ለምን ተቀጥረው መስራት እንደፈለጉ በጽሁፍ ገልፀው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • አመልካቾች የሙያ ብቃት በሚያስፈልጋቸው የትምህርት ዝግጅት የብቃት ማረጋገጫ በማስታወቂያው በተጠየቀው የትምህርት ደረጃ ልክ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • የሙያ ብቃት ምዘና ያልተጀመረባቸው የትምህርት መስኮች ከሚመለከተው ተቋም የሙያ ብቃት አለመጀመሩን ማስረጃ ካቀረቡ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
  • የኮንትራት ቅጥሩ ለ6 ወር ሆኖ እንደአስፈላጊነቱ በየ6 ወሩ ይታደሳል፡፡
  • ተወዳድሮ ያለፈ የስራ ተያዥ/ዋስ/ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  • ፈተና የሚሰጥበት ቀንና ቦታ በሌላ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡
  • አመልካቾች የምትመዘገቡበት ሊንክ በዌብሳይታችን ameco.et ማግኘት ትችላላችሁ ወይም ይህ ሊንክ በመጫን ይመዝገቡ

 https://forms.gle/wUye63btqpfmTR677 መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

  • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-226-50-07 ደወለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

ባሕር ዳር

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here