በድጋሚ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
27

የደብረ ማርቆስ አጠቃላይ ስፔሻላይድ ሆስፒታል በ2019 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል የተኝቶ ታካሚ ህሙማን የምግብ አቅርቦት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የንግድ ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. የግዥ መጠኑ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሽህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ኦርጅናሉን ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ የደረሰኘን ፎቶ ኮፒ ከፋይናንስ ወይም ከዋጋ ማቅረቢያ ፖስታ ውስጥ አስገብቶ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀን በጋዜጣ ቆይቶ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ 8፡30  ይከፈታል፡፡
  5. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ የስብሰባ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡
  7. የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጨረታዉ ከተከፈተበት ቀን አንስቶ የሚቆጠር ዝቅተኛ ቀን ከ40 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
  11. የጨረታ ሰነዱ ሥርዝ ድልዝ መሆን ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፡፡
  12. የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለዉጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታዉ ራሳቸዉን ማግለል አይችሉም፡፡
  13. ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከግ/ፋ/ን/አ/ደ/የስ/ሂደት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 771 22 46 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የደብረ ማርቆስ/አጠ/ስፔ/ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here