ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
19

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ደብረታቦር ከተማ የሚገኘው የጎህ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዪን ኃ.የተወሰነ ሎት 1. ብትን ጨርቅ የሀገር ውስጥ ታይዋን 308 ሜትር፣ ሎት 2. የሀገር ውስጥ ቱርክ ሸሚዝ ብዛት የወንድ 70፣ የሴት ብዛት 4፣ ካፖርት የሱፍ ብሉ ብላክ ብዛት 5፣ ካኪ ቱታ ብዛት 92፣ ከጨርቅ የተሰራ ክብ ቆብ ብዛት 20፣ ሎት 3. የወንድ አጭር ጉርድ ቆዳ ጫማ በጥንድ ብዛት 82፣ የሴት አጭር ጉርድ ጫማ በጥንድ ብዛት 4፣ የፕላስቲክ ቦት ጫማ 88፣ ሎት4. ጎግል መነጽር ብዛት 10፣ የእጅ ጓንት ብዛት 34 ጥንድ፣ ሎት 5. የተለያዩ የእንስሳት መድሃኒቶች፣ ሎት 6. የተለያዩ ፀረአረም እና ፀረ ተባይ ኬሚካሎች፣ ሎት 7. የተለያዩ የአትክልት ዘር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት (ግለሰብ) መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የተሰማሩና የዘመኑ  የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (ዋስትና) ወይም በጥሬ ገንዘብ ሁኖ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በጎሕ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ ዩኒዩን ኃ.የተወሰነ በሚል ስም በማሰራት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱን ወይም በጥቅል (ሎት) የሚገዛው እቃ እንጅ በአንድ ማስታወቂያ ሎት አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
  5. ተጫራቾች የሚገዙ እቃዎችን አይነት፣ መጠን እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) የሚገልጽ የጨረታ ሰነዱን እና የተጫራቾች መመሪያውን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከጎህ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዩን ኃ.የተወሰነ ቀርበው በመግዛት የመወዳደሪያ ዋጋ፣ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች ከታራ ቁጥር 1-5 የተዘረዘሩትን ሰነዶች ሞልተው በፖስታ በማሸግ በዩኒዩኑ ቢሮ ደብረታቦር በጣይቱ ክ/ከተማ ቀበሌ 01 ፀደይ ባንክ ደ/ታበር ዲስትሪክት ህንጻ 1ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት በ3 ቀን ውስጥ ያሸነፈበትን ዕቃዎች ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. አሸናፊው የሚለየው በሎት (በምድብ) ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ይሆናል፡፡ ከሎት ውስጥ የአንዱ ዕቃ ዋጋ ካልሞሉ ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ፡፡
  9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ እስከ 6፡30 ጨምሮ የጨረታ ሰነዱ ተሸጦ በ10ኛው ቀን የመጨረሻ ከቀኑ 8፡30 ላይ ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡40 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡

ጎሕ ሁለገብ የገ/ህ/ማ/ዮኒየን/ኃ.የተ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here