በመኖሪያ ቤት ውስጥ የተገኘው ድብ

0
49

በአሜሪካ ኮሎራዶ የላቭላንድ ቀጣና ኗሪዋ ድመታቸው ከቤት  ውጪ እንድትንቀሣቀስ ከፍተው በተዉላት በር ድብ ገብቶ ፊት ለፊት መፋጠጣቸውን  ናይን ኒውስ ድረ ገጽ ባለፈው ሳምንት ለንባብ አብቅቶታል፡፡

ሊን ፊልድማን የተሰኙት ሴት ከቀናት በፊት የኮሎራዶ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣናት በቀጣናው በተከሰተው ድርቅ የዱር እንስሳት በተፈጥሯዊ መኖሪያቸው የሚበሉት በማጣታቸው ወደ ሰዎች መኖሪያ ሊገቡ እንደሚችሉ እና ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ማሳሰቡን አስታውሰዋል፡፡

ሊን ፊልድማን ቀደም ባሉት ጊዜያት መኖሪያ ቤታቸው በኩሬ አቅራቢያ በመሆኑ አልፎ አልፎ የዱር እንስሳት በግቢያቸው ይመለከቱ ነበር፡፡ በእለቱ ወደ ቤታቸው ዘልቀው መተላለፊያውን ሲመለከቱ  ግን ከድቡ ጋር ይፋጠጣሉ፡፡ ድብ ሲያዩ የመጀመሪያ ጊዜያቸው በመሆኑም መደናገጣቸውን አልሸሸጉም፡፡

ድቡን እንደተመለከቱት የተራበ አለመሆኑን ተገንዝበዋል፤ ጀነን ብሎ ወደ ሚቀጥለው ክፍል ሲገባም በቀጥታ ወደ ስልካቸው አምርተው ለፖሊስ 911 የድረሱልኝ ጥሪ ያሰማሉ፡፡ ኗሪዋ ድቡ በቤታቸው ውስጥ እንዳለ ፎቶ ግራፍ ማንሳት አልቻሉም ነበር፡፡ ጐረቤቶቻቸው ግን ውጪ ድቡን ባዩበት ወቅት በቪዲዮ መቅረጻቸውን ኋላ ላይ ተረድተዋል፡፡

የርዳታ ጥሪ የተደረገለት የፖሊስ ጣቢያም አባላቱን ልኮ በቦታው እንደደረሱ           ድቡ ከአካባቢው መራቁን ለሊን ፊልድማን አስረድተዋቸዋል፡፡ ጥቂት ቆይተው ሊንድ ማን ዙሪያቸውን ሲያማትሩ ለድመቷ የቀረበላት ምግብ ሙሉ በሙሉ ተበልቷል፡፡

የኮሎራዶ የፓርክ እና የዱር እንስሳት ጥበቃ ቃል አቀባይ ካራቫን ሁስ ድቦች ለኃይል ምንጭ የሚያስፈልጋቸው የምግብ መጠን በርካታ በመሆኑ ትርፍራፊ፣ የሚጣል ተረፈ ምግብ ፍለጋ በሰዎች መኖሪያ ቀጣና እንደሚዘልቁ  ነው ያስታወቁት፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር  የነሐሴ  4  ቀን 2018 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here