ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
23

በአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ የአዲስ አለም ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል ሎት 1. የህሙማን ምግብ አቅርቦት አውት ሶርስ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡- መስፈርቱን የሚያሟሉ መሣተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡ እና QR code ደረሰኝ እንዳሸነፈ የክፍያ ሰነድ ማቅረብ የሚችል፡፡
  5. በጨረታው ለመሳተፍ የሁለት ዓመት የሥራ ልምድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ከግ/ፋ/ንብ/አስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ዝርዝር መግለጫ ወይም (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩ ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሰፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  10. ጨረታው ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን 3፡00 ተዘግቶ በዚያው ቀን ከቀኑ 8፡00 ይከፈታል፡፡
  11. አሸናፊ ማሸነፋን ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በቁርጥ ብር 80,000 (ሰማኒያ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሰፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ የውል መያዥ ማስያዝ አለበት፡፡
  12. ማንኛውም ተጫራች ሀሳቡን በታሸገ ፖስታ በአዲስ አለም ሆስፒታል ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ደ/ የስራ ማስገባባት ያለባቸው ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ተዘግቶ 8፡00 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን በሰዓቱ የማገኙ ከሆነ ጨረታው በዚያው ቀን እና ሰዓት በጨረታ ኮሚቴው ይከፈታል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. የጨረታ ውድድሩ አሸናፊ የሚለየው በጠቅላላ ሎት ድምር ውጤት ነው፡፡
  15. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በአካል በገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 218 10 34 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአዲስ አለም ሆስፒታል

ባሕር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here