በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የአገዉ ግምጃ ቤት ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የሶላር እና የኤሌክትሮ መካኒካል ዕቃዎች አቅርቦት ግዥ ለመግዛት ስለሚፈልግ የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ፎቶ ኮፒ አያይዘዉ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት ፎቶ ኮፒ አያይዘዉ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ከአገዉ ግምጃ ቤት ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በድርጅቱ ባንክ ገቢ በማድረግ ደረሰኝ በማምጣት በመ/ቤታችን መሂ-1 የሞሉትን ዋጋ 2 በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአገዉ ግምጃ ቤት ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ገቢ/ግ/ፋ/ን/አስ/ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 02 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም በአገዉ ግምጃ ቤት ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ነሐሴ 18/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 2/2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን በ16ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4፡15 ታሽጎ ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን ብሔራዊ በዓል ወይም እሁድ ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ስርዝ ድልዝ ለማንበብ አስቸጋሪ የሆነ ሰነድ አሞላል ተቀባነት የለዉም፡፡
- ጨረታዉ ቴክኒካል ጉዳዮችን በሰነድ ላይ ያሉትን በማሟላት ማለፍ አለበት፡፡
- አሸናፊዉ አካል ለዉል ማስከበሪያ 10 በመቶ በባንክ የተመሰከረለት (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በድርጅቱ ባንክ ገቢ በማድረግ ደረሰኝ በማምጣት በመ/ቤታችን መሂ-1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ የሆነ ድርጅት ዕቃዉን እስከ አገዉ ግ/ቤት ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድረስ በራሳቸዉ ወጪ ማምጣት እና በባለሙያ በማስፈተሽ ወይም በማስመርመር ገቢ ማድረግ አለባቸዉ፡፡
- የተያዘ የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊ ድርጅቱ ዉል እንደተያዘ ለተሸናፊዎች ተመላሽ ይሆናል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ስለ ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 224 04 62 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአገው ግምጃ ቤት ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

