የፍኖተ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል ከወረቀት ነጻ የሆነ ህክምና ለመስጠት የፉል አዉቶ ሚሽን (ሙሉ ኔትወርኪግ) ሶፍት ዌር ለመግዛት ሶፍት ዌር አቅራቢዎችን በመጋበዝ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የአንድ ጊዜ የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከታወቀ የመንግስት ሆስፒታል ላይ የፉል አዉቶሜሽን (ሙሉ የኔትወርክ) ሥራ ለመስራታቸዉ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- አሸናፊ የሚሆነዉ የሶፍት ዌር አቅራቢ ሶፍት ዌሩን ከሰራ (ከዘረጋ) በኋላ ለ3 ወር ስልጠና የሚሰጥ እና የሚአበቃ ይሆናል፡፡ አሸናፊዉ ለሰራተኛዉ ስልጠና ከሰጠ በኋላ ለ6 ወር ክትትል ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
- ሸናፊው ተጫራች የሚሰራውን የሶፍትዌር አፕሊኬሽን (executable application)፣ የተቀናጀውን ዳታቤዝ (configured database) ለሆስፒታሉ የሚያስረክብ ይሆናል፡፡ እንዲሁም ሶፍትዌሩ ከሆስፒታሉ ነባር የጤና መድህን አስተዳደር ሲስተም እና ከሌሎች የሚመለከታቸው የላይዘን ሲስተሞች ጋር መገናኘት /መተሳሰር የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ ጋር በተያያዘው የዋጋ መሙያ መሰረት ዋጋ በመሙላት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው በቀረበው ዝርዝር መሠረት በእያንዳንዱ ሎት በጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው
ድርጅት ሲሆን በጥቅል ድምር አሸናፊ ለሚለይባቸው ግዥዎች ለአንድም ግዥ ዋጋ አለመሙላት ከጨረታ ውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡ - ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የፋይናንስ ቡድን ቢሮ በመሄድ ለሰነዱ የመጫረቻ ሰነድ እያንዳንዳቸውን በብር 100 (አንድ መቶ ብር) ገዝተው መጫረት ይችላሉ፡፡ አሸናፊዉ ክፍያ የሚከፈለዉ ለ1 ዓመት የሚቆይ 5 በመቶ ሪቴሽን ተሰልቶ የሚቆረጥ እና ቀሪዉ ክፍያ በ3 ጊዜ የሚከፈል ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና በፍ/ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በፍ/ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፍ/ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል በ3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ እለቱ ቅዳሜና እሁድ ወይም ህዝባዊ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ማስያዝ እና አገልግሎት ወጭ ችሎ ማስረከብ አለበት፡፡
- መስሪያ ቤቱ 20 በመቶ ከግዥዉ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡ የተሻለ አማራጭ ካገኘም ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በማስታወቂያው ላይ ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ በፋክስ ቁጥር 058 775 13 32 መላክ እንዲሁም በስልክ ቁጥር 058 775 00 16 /058 775 00 63 /058 775 10 16 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የፍኖተ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል

