በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ  ማስታወቂያ

0
36

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል ለ2019 በጀት  ዓመት ሎት 1. የህክምና ኦክስጅን ግዥ በድጋሚ ለ1 አመት፣ ሎት 2. የሰራተኞች ማመላለሻ  የመኪና ሰርቪስ አገ/ት ግዥ በድጋሚ ለ1 አመት፣ ሎት 3.  የደረቅ ጭነት  መኪና  ኪራይ አገ/ት ግዥ በድጋሚ ለ1 አመት፣ ሎት 4 የመድኀኒት እና የላብራቶሪ የሬጀንትቶች ግዥ ለ6 ወር እና ሎት 5 የሲቲስካን ክፍክ የሪኖቬሽን  ስራ እና ሌሎች አዳዲስ ስራዎችን   በግልጽ  ጨረታ አወዳድሮ   መግዛት ወይም ማሰራት  ይፈልጋል፡፡

  1. በሎት አምስት የሚጫረቱ ተጫራቾች ደረጃ ስድስት እና በላይ የግንባታ የብቃት ማረጋገጫ ለመስጠት ስልጣን ከተሰጠዉ መንግስታዊ አካል  የብቃት ማረጋገጫ የተሰጣቸዉ እና በህንፃ ግንባታ ዘርፍ ተሰማርተዉ ከብር 5,000,000 (አምስት ሚሊዮን ብር)  እና በላይ ፕሮጀክት ስራ አጠናቀዉ ዉል ለፈፀሙበት መ/ቤት ወይም ድርጅት ማስረከባቸዉን የሚገልጽ የጽሁፍ መረጃ /Testimonial  letter/ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ  እና በሎት 4. ላይ የሚጫረቱ ተጫራቾች  ሜዲካል ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ካርድ/ሰርተፊኬት እና ከመንግስት የሚጠበቅባቸዉን የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸዉ ማስረጃ የግብር ክሊራንስ  ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የግዥዉ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን  የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ኮፒ  ከጨረታ  ሰነዱ ጋር አያይዘው  ማቅረብ  ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ስለጨረታው አጠቃላይ ዝርዝር  መግለጫ (ስፔስፊኬሽን)  እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር   የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ   በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 3  መዉሰድ የሚቻል ሲሆን ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ  እስከ 15ኛዉ ቀን ድረስ እስከ 11፡30 ብቻ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በልዩ ልዩ  ምክንያት  በሚመለከታቸው የመንግስት  ተቋማት  ያልታገዱ  መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸዉን በአማረኛ ቋንቋ ማንኛውንም የመንግስት ግብር ያካተተ ሆኖ  የጨረታ ሰነዱ  በፖስታ ታሽጎ   የድርጅቱ ክብ  ማህተም፣ ፊርማ እና አድራሻ  ማስቀመጥ  አለባቸዉ፡፡ በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት  ስርዝ ድልዝ ማድረግ የለባቸዉም፡፡ የጨረታ ሰነዱን  ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀዉ  የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ  ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ  ማስከበሪያ  ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ማንኛዉንም የመንግስት ግብር ጨምሮ  በሎት 1. እና በሎት 2. ላይ   የሞሉትን ጠቅላላ ድምር አንድ በመቶ፣ በሎት 5. ላይ ሁለት በመቶ በሎት  ላይ   ብር 30,000 (ሰላሳ ሽህ ብር)፣ በሎት 3. ብር 10,000 (አስር ሽህ ብር) ብቻ በባንክ የተረጋገጠ  የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከፖስታው ውስጥ  አብሮ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
  10. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸዉ ከታወቀ የዉል ማስከበሪያ ማንኛዉንም የመንግስት ግብር ጨምሮ በሎት 1. በሎት 2. እና በሎት 5. ላይ የሞሉትን ጠቅላላ ድምር 10 በመቶ፣ በሎት 4. ላይ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሽህ ብር) እና በሎት 3. ብር 20,000 (ሃያ ሽህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ  የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሆስፒታሉ የጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  11. የጨረታዉ አሸናፊ የሚለየዉ ከመድሀኒት ግዥ በስተቀር በሎት ይሆናል፡፡
  12. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆይና በ16ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ተጫራቾች  ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው  በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙ  ግን ፕሮግራሙ  የማይስተጓጎል  ይሆናል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት  ቀን በዓል ከሆነ  በሚቀጥለው  የመንግስት የሥራ ቀን  በተጠቀሰው  ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  13. ተጫራቾች እቃዉን በራሳቸው ትራንስፖርት እስከ እንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል ድረስ በማምጣት  የሚያስረክቡ ይሆናል፡፡
  14. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ  በሙሉ  የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ 058 827 04 27 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here