እየጠፋ መልሶ የሚገኘው ደሴት

0
106

በካናዳ ብሪቲሽ ኮሎምቢያ ግዛት ከማካንዚ በስተሰሜን በሚገኝ የውኃ ማጠራቀሚያ ኃይቅ ወይም ግድብ ላይ በሀምሌ ወር አጋማሽ የታየ ደን የለበሰ ደሴት በነሀሴ ወር መግቢያ ከእይታ መሰወሩን ዩፒአይ ድረ ገጽ ባለፈው ሳምንት አስነብቧል፡፡

የብሪትሽ ኮሎምቢያ የዉኃ ሀብት ቃል አቀባይ ቦብ ጋመር መጀመሪያ አካባቢ የተለቀቁ ምስሎች በ “ኤ አይ” የተቀናበሩ ሊሆኑ እንደሚችሉ ቢጠረጥሩም በኋላ ላይ ስፋቱ 105,486 ስኩዌር ጫማ የተለካ በደን የተሸፈነ ደሴት ሀምሌ 13/2018 ዓ.ም ወይም /ጁላይ 20/2026/ እ.አ.አ ከሳተላይት በተወሰደ  ምስል  መታየቱን ማረጋገጥ ችለዋል፡፡

ሁለት ሳምንታት ዘግይቶም  ቀጣናውን ሲቃኙ  ባለሙያዎች የጠፋውን ደሴት ዳግም መመልከት መቻላቸውን አስታውቀዋል፡፡

ቃል አቀባዩ ቦብ ጋመር የደሴቱን  መጥፋት እና በድጋሚ መታየት አስመልክተው በሰጡት ሙያዊ አስተያየት ደሴቱ ከታቆተው ኃይቅ ዳርቻ ተገንጥሎ የወጣ መሆኑን ነው ያብራሩት፡፡ በዳርቻው ይዞት የመጣውን ዓፈር እና በጊዜ ብዛት የሚበሰብሱ ዛፎች እና ቅጠላ ቅጠል ስር እንዲይዝ እያስቻሉት የሀይቁ ውኃ መጠኑ ሲጨምር ዳርቻውን ለቆ መሀል ላይ እየተንሳፈፈ፣ የውኃ ከፍታ መጠኑ ሲቀንስ ከዳርቻው ጋር ተገናኝቶ በመመሳሰል የጠፋ  እንደሚመስል ነው በማጠቃለያነት ያስረዱት፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የመስከረም 4  ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here