በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አንቀፅ 366 (1)፣ 367 (1) እና 372 መሰረት የጣና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ የባለ አክሲዮኖች 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እሁድ ጥቅምት 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በሙሉዓለም የባሕል ማዕከል የመሰብሰቢያ አዳራሽ ስለሚያካሂድ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጠቅላላ ጉባዔው እንዲገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
የማኅበሩ ዓይነት የአነስተኛ የፋይናንስ ሥራ ላይ የተሰማራ አክሲዮን ማኅበር ነው፡፡
- የማኅበሩ የተከፈለ ካፒታል………….. 104,595,000.00
- የማኅበሩ የምዝገባ ቁጥር……………. AM/BD/3/0000833/2011
- የማኅበሩ ድረ-ገፅ……………………. www.tanamfi.com
የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች፡-
- የጉባዔውን አጀንዳዎች ማጽደቅ፤
- አዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበልና ማጽደቅ፤
- በነባር በባለአክሲዮኖች የተገዙ ተጨማሪ አክሲዮኖችን መቀበልና ማጽደቅ፤
- የዳይሬክተሮች ቦርድ የ2025/26 ሒሳብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ክንውን ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ፤
- የውጭ ኦዲተሮችን የ2025/26 ሒሳብ ዓመት ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ፤
- ከ2019 እስከ 2021 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ዓመታት የሚያገለግሉ የውጭ ኦዲተር መሾም እና ክፍያቸውን መወሰን፤
- በ2025/26 ሒሳብ ዓመት በተገኘው ትርፍ ክፍፍል ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ፤
- የ2025/2026 ሒሳብ ዓመት ከተገኘው ትርፍ ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የድካም ዋጋ መወሰን፤
- የጉባዔውን ቃለ-ጉባኤ ማጽደቅ፣
ማሳሰቢያ፡- በጉባኤው ለመሳተፍ ስትመጡ በዘመኑ የታደሰ መታወቂያ እንድትይዙ እና በጉባኤው መገኘት ለማትችሉ ባለአክሲዮኖች ከጉባኤው 3 ቀናት በፊት የዘመኑ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ባሕር ዳር ከተማ አጼ ሰርፀ ድንግል ት/ቤት ጀርባ በሚገኘው በዋና መስሪያ ቤቱ ጽ/ቤት ወይም በተቋሙ ቅርንጫፎች በአካል በመገኘት እንድትወክሉ ወይም ስልጣን ባለው የመንግስት አካል ተረጋግጦ የተሰጠ የውክልና ሰነድ በመያዝ በስብሰባው ላይ እንድተገኙ ጥሪውን ያስተላለፋል፡፡
የማኅበሩ ዋና መ/ቤት አድራሻ፡-……… ባሕር ዳር ከተማ ፋሲሎ ክ/ከተማ ቀበሌ 03 የቤት ቁጥር B66 አጼ ሰርፀ ድንግል ት/ቤት ጀርባ ነው፡፡
የዳሬክተሬቶች ቦርድ

