የመድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ደሴ ቅርንጫፍ በምሥራቅ አማራ ለሚገኙ ሆስፒታሎች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ የመከላከያ ሰራዊት፣ ለመንግስት ሆሰፒታሎች፣ ለዩንቨርስቲ ሆስፒታሎች፣ ለዞን ጤና መምሪያዎችና ለወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤቶች መድሃኒትና የህክምና ቁሳቁሶች፣ ኬሚካሎችና ሪኤጀንቶች እንዲሁም ሌሎች በመ/ቤቱ የሚታዘዙ እቃዎች አጓጉዞ ተቋማቱ ድረስ ማድረስ አንዲቻልና የህብረተሰቡን ጤና ለማሻሻል ለምናደርገው ርብርብና ስኬታማነት ጥራት ያላቸው ተሽከርካሪዎች የሚያቀርቡ፣ ተጠያቂነትን የሚቀበሉና ኃላፊነትን የሚወስዱ፣ በጨረታውና በውለታቸው መሰረት ብቻ የሚሰሩ፣ ኃላፊነትን የሚቀበሉና በህግ ስርዓት የሚመሩ የጭነት አጓጓዥ ድርጅቶችን የግልጽ ጨረታ በማውጣትና ኮንትራት ውል በመያዝ የመድሃኒትና ህክምና መሳሪያዎች የሚያጓጉዝ ደርጅት ይፈለጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን በመመሪያ ከፀደቀውና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ነገር ግን ከላይ ከተራ ቁጥር የተጠቀሱትን ያላቀረቡ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሉት 25 (ሃያ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ጢጣ በሚገኘው በጠቅ/አገ/ንብ/አስተዳደር የሥራ ክፍል በአካል በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከመክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) አንድ በመቶ በባንክ በተመሰከረለት (ሲፒኦ) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን ደረቅ ቼክ ማስያዝ አይቻልም፡፡
- በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 25 ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ድረስ ለዚሁ ስራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ከጠዋቱ 2፡30 ተዘግቶ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 3፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጢጣ በሚገኘው በመ/ቤቱ ቅጥር ግቢ ጥቅምት 13/2019 በይፋ ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የጨረታ ውድድሩን የሚያካሂደው በነጣላ ዋጋ ዝቅተኛ ዋጋ ባቀረበ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ቢፈልጉ ጢጣ በሚገኘው በጠቅ/አገ/ንብ/አስተዳደር የሥራ ክፍል በግንባር ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 033 115 05 53 በመደውል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኢትጵያ መድኃኒት አቅራቢ ድርጅት ደሴ ቅርንጫፍ

