በምስራቅ ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ ስር የሚገኘው የጎዘምን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2019 ዓ/ም ሎት 1. ጀኔሬተር፣ ሎት 2. የውጭ ስሪት ተተካይ የአዳራሽ ወንበር እና ሎት 3. የአገር ውስጥ ስሪት የአዳራሽ ሸራተን ወንበር ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድና የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸውና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥ መጠናቸው ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ግዥዎች የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈልና ገንዘብ ያዥ ላይ ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ጎዛምን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት ማለትም በሎት 1. የሚወዳደሩት ብር 100,000 (አንድ መቶ ሽህ ብር)፣ በሎት 2. የሚወዳደሩት ብር 40,000 (አርባ ሽህ ብር) እና ለሎት 3. የሚወዳደሩት ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሽህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ከዋጋ መሙያ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ የጨረታ ሰነድ ሲሸጥ ይቆይና በ11ኛው ቀን 3፡50 ታሽጎ ከቆየ በኋላ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡
- በጨረታ ላይ የተሳተፉ ተጫራቾች በራሳቸው ግላዊ ችግር ምክኒያት በመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ባይገኙም ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
- ተጫራቾች በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ተዘጋጅቶ የተሰጣቸውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ የይዘት ለውጥ ወይም ማሻሻያ ሳያደርጉ ዋጋ ብቻ ሞልተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው መደበኛ የጨረታ ሰነድ ላይ ተጫራቾች የግልጽነት ማብራሪያ ካስፈለጋቸው በአካል ቀርበው በፁሁፍ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ዋጋ የሞሉበትን ሰነድ ለብቻው በአንድ ፖስታ፣ የጨረታ ማስከበሪያውን ለብቻው በሌላ ፖስታ በማድረግ ሁለቱን ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ በማስገባት ስምና አድራሻቸውን በመፃፍ የድርጅቱን ማህተም በመርገጥ ከጨረታ መዝጊያው ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙ እቃዎችን ዝርዝር መግለጫ (የተፈላጊነት ደረጃ) በግዥ ቡድናችን ከተዘጋጀው መደበኛ የጨረታ ሰነድ ላይ ማየት ይችላሉ፡፡ ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ግዥዎች የግዥ ቡድናችን የሚያቀርብ ይሆናል፡፡
- ግዥ ፈፃሚውን መ/ቤት የጨረታ ውድድሩን በሎት ዋጋ (በጥቅል ዋጋ ድምር) የሚያወዳድር ይሆናል፡፡ በርክክብ ወቅት በባለሙያ መረጋገጥ የሚገባቸው ዕቃዎች በባለሙያ እየተረጋጋጡ የምንረከብ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 178 01 30 /058 771 14 22 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጎዛምን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

