በምዕ/ጐጃም ዞን ለፊቤላ ኢንዱስትሪ ኃ/የተወሰነ የግል ማህበር በቡሬ ከተማ ለፋብሪካዎች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 01. የፅሀፈት እቃዎች እና ሎት 02. የፅዳት እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የእቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን )ከጨረታ ሰነዱና በናሙና የቀረቡትን ማግኘት ይችላሉ ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል ከሀገር ዉስጥ ግዥ ዋና የስራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 03 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የስራ ቀናት ማለትም ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ጠዋት ከ 2፡00 እስከ 6፡00 እና ከሰአት ከ 7፡30 እስከ 11፡30 ማግኘት ይችላሉ ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ከሀገር ዉስጥ ግዥ ዋና የስራ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ጠዋት ከ 2፡00 እስከ 6፡00 እና ከሰዓት ከ 7፡30 እስከ 11፡30 ድረስ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የስራ ቀናት እና በ16 ኛዉ ቀን እስከ ጠዋቱ 4፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሀገር ዉስጥ ግዥ ዋና የስራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 03 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተወደዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ጨረታዉ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሆኖም የሚከፈትበት ቀን ህዝባዊ በዓል ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በሀገር ዉስጥ ግዥ ዋና የስራ ክፍል ቢሮ ቁጥር ዐ3 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 09 10 69 31 95/ 09 13 60 61 13 በመደወል ማግኘት ይችላሉ ፡፡
ፊቤላ ኢንዱስትሪ ኃ/የተወሰነ የግል ማህበር

