በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የኮምፒዩተርና ተዛማጅ መሳሪያዎችን ከ ILO በተገኘ የድጋፍ በጀት ለ3ኛ ጊዜ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥው መጠን ብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ መተማመኛ ቅፅ (ክፍል 4) ሞልተው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማረጋገጫ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተ.ቁ. 1-6 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ፣ የጨረታ ማስከበሪያቸውን እና ቴክኒካል ሰነዳቸውን በአንድ ፖስታ በማሸግ እንዲሁም የፋይናንሻል ሰነዳቸውን በሌላ ፖስታ በማሸግ ለየብቻ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ግዥ የሚፈፀምላቸውን እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ ፡፡ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ሎት ብር 70,000 (ሰባ ሽ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒዩ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡ የልዩ አስተያየት ተጠቃሚ የሆኑ ድርጅቶች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ካደራጃቸው ተቋም የተሰጠ (በሃላፊ የተፈረመ) የድጋፍ ደብዳቤ ይሆናል፡፡ ከተጫራቾች የሚቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን ቢያንስ ለተጨማሪ 28 ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከመስከረም 25/ 2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 4/2019 ዓ.ም ለ10 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ባህር ዳር በሚገኘው የአብክመ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ቁጥር 20 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ጥቅምት 4/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 20 ውስጥ በይፋ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰአት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በጥቅል (በሎት) ዋጋ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበት እያንዳንዱ ቅፅ ላይ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ፡፡ አለማድረግ ከጨረታ ውድድር ውጪ ያስደርጋል፡፡
- በአንድ ሎት ላይ በከፊል ዋጋ ሞልቶ መወዳደር ከዋጋ ውድድር ውጪ ያስደርጋል፡፡
- በዋጋ መሙያ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ፡፡ አለማድረግ ከውድድር ውጪ ያስደርጋል ፡፡
- የርክክብ ቦታው በአብክመ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ዋናው እቃ ግምጃ ቤት ውስጥ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
- ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ወይም ማብራሪያ መጠየቅ ቢፈልጉ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 5ኛው ቀን ድረስ ብቻ በ058 320 68 56 በመደወል ወይም በአካል በመምጣት ማግኘት ይችላሉ ፡፡
የአብክመ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ
ባህር ዳር

