ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
59

በሰሜን ጐጃም አስተዳደር ዞን የሰሜን ሜጫ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለሰሜን ሜጫ ወረዳ እንሰሳትና ዓሳ ሃብት ጽ/ቤት የእንሰሳት መድሃኒት በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሰለዚህ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች  መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፋ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የሞሉት ጥቅል ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የእንሰሳት መድሃኒቱን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ በሰሜን ሜጫ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥ/ንብ/አስ/ ቢሮ ቁጥር 07 መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ11ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 11ኛዉ ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር አንድ በመቶ ወይም የመድሃኒቱን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋሰትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሰሜን ሜጫ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥ/ንብ/አስ/ ወይም ቢሮ ቁጥር 07 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው የመዝጊያ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. በጨረታው መክፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት አለባቸው፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው ባይገኙ ጨረታው ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡ ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ ኃላፊነት አይወስደም፡፡
  12. ተጫራቾች በዋጋ መሙያው ላይ ማህተምና ፊርማ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
  13. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 38 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 330 04 32 /058 330 01 96 /058 330 04 48 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሰሜን ሜጫ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here